Loading
Singer
አዝ፦ ምን ፡ ይሳንሃል ፡ ምን ፡ ያቅትሃል ሁሉ ፡ ይቻልሃል ፡ ሁሉ ፡ ይቻልሃል ምን ፡ ይሳንሃል ፡ ምን ፡ ያቅትሃል ሁሉ ፡ ይቻልሃል ፡ ሁሉ ፡ ይቻልሃል ጌታ ፡ ሆይ ፡ ለአንተ ፡ ምን ፡ ይሳንሃል ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ ለአንተ ፡ ምን ፡ ያቅትሃል (፪x) የእስራኤልን ፡ ሕዝብ ፡ ከባርነት ፡ ምድር በውኑ ፡ ሊያወጣ ፡ ሙሴ ፡ ማን ፡ ነበር አፌን ፡ በአፍህ ፡ ላይ ፡ አደርጋለሁ ፡ ብለህ ላክኸው ፡ ወደ ፡ ፈርዖን ፡ ኮልታፋውን ፡ መርጠህ በችሎታህ ፡ ታምነህ ፡ ይህን ፡ ትሰራለህ ይህን ፡ ታደርጋለህ (፪x) አዝ፦ ምን ፡ ይሳንሃል ፡ ምን ፡ ያቅትሃል ሁሉ ፡ ይቻልሃል ፡ ሁሉ ፡ ይቻልሃል ምን ፡ ይሳንሃል ፡ ምን ፡ ያቅትሃል ሁሉ ፡ ይቻልሃል ፡ ሁሉ ፡ ይቻልሃል ጌታ ፡ ሆይ ፡ ለአንተ ፡ ምን ፡ ይሳንሃል ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ ለአንተ ፡ ምን ፡ ያቅትሃል (፪x) ብዙ ፡ የተማሩ ፡ አዋቂዎችን ፡ ትተህ ዓሣ ፡ አጥማጆችን ፡ ለራስህ ፡ መረጥህ እጅግ ፡ ታናናሾች ፡ ተራ ፡ በተባሉት ዓለምን ፡ አዳረስክ ፡ በወንጌልህ ፡ እሳት በችሎታህ ፡ ታምነህ ፡ ይህን ፡ ትሰራለህ ይህን ፡ ታደርጋለህ (፪x) አዝ፦ ምን ፡ ይሳንሃል ፡ ምን ፡ ያቅትሃል ሁሉ ፡ ይቻልሃል ፡ ሁሉ ፡ ይቻልሃል ምን ፡ ይሳንሃል ፡ ምን ፡ ያቅትሃል ሁሉ ፡ ይቻልሃል ፡ ሁሉ ፡ ይቻልሃል ጌታ ፡ ሆይ ፡ ለአንተ ፡ ምን ፡ ይሳንሃል ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ ለአንተ ፡ ምን ፡ ያቅትሃል (፪x) ልባቸው ፡ ሲቀልጥ ፡ በዮርዳኖስ ፡ ሙላት ታቦት ፡ ተሸክሙ ፡ እነዚያ ፡ ካህናት በተንጣለለው ፡ ወንዝ ፡ ሰገባ ፡ እግራቸው ለሁለት ፡ ከፍለህ ፡ አንተ ፡ አሻገርካቸው በችሎታህ ፡ ታምነህ ፡ ይህን ፡ ትሰራለህ ይህን ፡ ታደርጋለህ (፪x) አዝ፦ ምን ፡ ይሳንሃል ፡ ምን ፡ ያቅትሃል ሁሉ ፡ ይቻልሃል ፡ ሁሉ ፡ ይቻልሃል ምን ፡ ይሳንሃል ፡ ምን ፡ ያቅትሃል ሁሉ ፡ ይቻልሃል ፡ ሁሉ ፡ ይቻልሃል ጌታ ፡ ሆይ ፡ ለአንተ ፡ ምን ፡ ይሳንሃል ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ ለአንተ ፡ ምን ፡ ያቅትሃል (፪x) ለመሞት ፡ ጥቂት ፡ ቀን ፡ የቀራትን ፡ አይተህ እንድትመግበው ፡ ደሃዪቱን ፡ አዘህ ከኮራት ፡ ፈፋ ፡ ውስጥ ፡ ጌታ ፡ አውጥተኸው በሰራፍታ ፡ ምድር ፡ ኤሊያስን ፡ መገብኸው በችሎታህ ፡ ታምነህ ፡ ይህን ፡ ትሰራለህ ይህን ፡ ታደርጋለህ (፪x)