Loading
Singer
ኢየሱስ ፡ ለኔ ፡ ሁሉን ፡ ነው ጌታዬ ፡ እርሱ ፡ በቂ ፡ ነው የሚያሻን ፡ የለም ፡ ጌታ ፡ አለኝ ሁሉ ፡ በሁሉ ፡ የሆንልኝ ምን ፡ ያሻኛል ፡ ምን ፡ ያሻኛል ፡ ምን ፡ ያሻኛል ጌታ ፡ ይበቃኛል ምን ፡ እሻለሁ ፡ ምን ፡ እሻለሁ ፡ ምን ፡ እሻለሁ ጌታን ፡ እግኝቻለሁ የሰማይ ፡ የምድር ፡ ጌታ በኃይሉ ፡ እጅግ ፡ የበረታ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ለኔ ፡ የተሰጠኝ በረከት ፡ ሙላት ፡ የሆንልኝ ብሩና ፡ ወርቁም ፡ የእርሱ ፡ ነው አምላኬ ፡ ሁሉን ፡ የፈጠረው እንደ ፡ ፈቃዱ ፡ የሆነው የአባቴ ፡ ፈቃድ ፡ ለኔ ፡ ነው የእርሱ ፡ የሆነው ፡ የእኔ ፡ ነው ወራሽ ፡ ነኝ ፡ ጌታ ፡ አባቴ ፡ ነው እንደ ፡ ባሪያ ፡ ሳሆን ፡ እንደ ፡ ልጅ ተቀብሎኛል ፡ እንደ ፡ ወዳጅ ለዚህ ፡ ጌታ ፡ እዜማለሁ በመንፈሥም ፡ እቀኛለሁ ለእርሱ ፡ ክብር ፡ ለእርሱ ፡ ምሥጋና ይኸው ፡ መዝሙር ፡ ታላቅ ፡ ነውና