Loading
Singer
ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ጌታዬ ፡ ጌታዬ ፡ ጌታዬ አምላኬ ፡ አምላኬ ፡ አምላኬ ምን ፡ እሻለሁ ፡ ባይኖችህ ፡ ታይቻለሁ ምን ፡ እሻለሁ ፡ በጆሮህ ፡ ተሰምቻለሁ ምን ፡ እሻለሁ ፡ በእጆችህ ፡ ተይዣለሁ ምን ፡ እሻለሁ ፡ በፊትህ ፡ ከብሬአለሁ የእግዚአብሔር ፡ መንፈስ ፡ ደስ ፡ የሚያሰኝ ፡ ደስ ፡ የሚያሰኝ ደስ ፡ የሚል ፡ መንፈስ ፡ ደስ ፡ የሚያሰኝ ፡ ደስ ፡ የሚያሰኝ የሚያረሰርስ ፡ ደስ ፡ የሚያሰኝ ፡ ደስ ፡ የሚያሰኝ ደስታን ፡ ይሞላል ፡ ይባርካል ሕዝቡን ፡ በእጆቹ ፡ ይዳስሳል የተራበች ፡ ነፍስ ፡ ትጠግባለች ፡ ያዘነችውም ፡ ትጽናናለች አዝ፦ የእግዚአብሔር ፡ መንፈስ ... ተራራው ፡ ሜዳ ፡ የሆነው በመንፈስ ፡ እንጂ ፡ መች ፡ በብርታት ፡ ነው ቁርጭምጭሚትን ፡ የምታጸና ፡ የሕዝብህ ፡ ጉልበት ፡ አንተ ፡ ነህና አዝ፦የእግዚአብሔር ፡ መንፈስ ... ሰላምህ ፡ ፈሰሰ ፡ እንደ ፡ ጅረት አርነት ፡ በዛ ፡ ባለህበት ደንዳናው ፡ ሁሉ ፡ ፈራረሰ በመንፈስህ ፡ ዘይት ፡ ረሰረሰ አዝ፦የእግዚአብሔር ፡ መንፈስ ...