Loading
Singer
ክብሩን ፡ ጥሎ ፡ እስከመስቀል ፡ ሞት ፡ እንደታዘዘህ ፡ እንደኢየሱስ ረብ ፡ ያልነውን ፡ ትምክህቱን ፡ እንደተወልህ ፡ እንደፓውሎስ በገዛ ፡ ዘመኑ ፡ ታዞ ፡ ሃሳብህን ፡ እንዳገለገለህ ፡ እንደዳዊት አዝ፦ አንተን ፡ መታዘዝ ፡ እፈልጋለሁ ፈቃድህን ፡ ላደርግ ፡ እሻለሁ አንተን ፡ መታዘዝ ፡ እፈልጋለሁ ፈቃድህን ፡ ላደርግ ፡ እሻለሁ ምን ፡ አደርግ ፡ ዘንድ ፡ ትወዳለህ (፬x) ፡ ትወዳለህ በግብጽ ፡ ካለው ፡ ክብር ፡ ይልቅ ፡ ሙሴ ፡ መከራውን ፡ መረጠ ብድራቱን ፡ ትኩር ፡ ብሎ ፡ ተመልክቶ ፡ ያንን ፡ አስመለጠ ለሃሳብህ ፡ ታዞ ፡ መንገድህን ፡ ይዞ ፡ እስከመጨረሻው ፡ ተከትሎህ ፡ ሮጠ አዝ፦ አንተን ፡ መታዘዝ ፡ እፈልጋለሁ ፈቃድህን ፡ ላደርግ ፡ እሻለሁ አንተን ፡ መታዘዝ ፡ እፈልጋለሁ ፈቃድህን ፡ ላደርግ ፡ እሻለሁ ምን ፡ አደርግ ፡ ዘንድ ፡ ትወዳለህ (፮x) ፡ ትወዳለህ