Loading
Singer
መልካም ፡ እረኛ ፡ መተማመኛ ኢየሱስ ፡ ሆንልኝ ፡ ለኔ ፡ ጉዳኛ ስጠማ ፡ ውሃዬ ፡ ስራብም ፡ ምግቤ ጠባቂዬ ፡ ነው ፡ ሆኖ ፡ አጠገቤ ነፍሱን ፡ ስለኔ ፡ ሰውቶልኛል ከክብሩ ፡ ወርዶ ፡ ተሰቅሎልኛል እንደርሱ ፡ ያለ ፡ ወዳጅ ፡ ከየት ፡ አገኛለሁ አዳኜን ፡ ውዴን ፡ እውደዋለሁ ዳገት ፡ ስወጣ ፡ አብሮኝ ፡ ይወጣል ሸለቆ ፡ ስወርድ ፡ እርሱ ፡ ያወጣኛል ሳዝን ፡ ስተክዝ ፡ ያበረታኛል ባሴት ፡ በደስታ ፡ ልቤን ፡ ይሞላል በመስቀል ፡ ጉዞ ፡ በፈተናዬ ይመራኛል ፡ ሆኖ ፡ መሪዬ በምድር ፡ ኑሮ ፡ በመከራዬ እርሱ ፡ ያጸናኛል ፡ ሆኖ ፡ አልኝታዬ በለምለሙ ፡ መስክ ፡ ያስድረኛል በእረፈት ፡ ውኃ ፡ ዘንድ ፡ ሁሌ ፡ ይመራኛል ብትር ፡ ምርኩዝህ ፡ ሁሌ ፡ ያጽናኑኛል አንት ፡ ከኔ ፡ ጋር ፡ ነህ ፡ ምን ፡ ያስፈራኛል