Loading
Singer
እንጀራ ፡ ልንበላ ፡ አልተከተልንህም ሃብት ፡ ብልጥግና ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ አልጠራንም ለምድር ፡ በረከት ፡ ታይቶ ፡ ለሚጠፋ መች ፡ ደምህ ፡ ፈሰሰ ፡ ለሚያልፍ ፡ ተስፋ የዘላለም ፡ ሕይወት ፡ ማግኘታችን ፡ ጉዳይ ሁሌም ፡ ብርቃችን ፡ ነው ፡ ከምን ፡ ጋር ፡ ሊተያይ ሕይወት ፡ ያካፈልከን ፡ ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ነህ ሌላ ፡ አላየንም ፡ በነፍሱ ፡ የጨከነ ግን ፡ ዛሬ ፡ ሲመጣ ፡ በየአደባባዩ ትኩረት ፡ የሚፈልግ ፡ የሚል ፡ እኔን ፡ እዩ አንተን ፡ አደብዝዞ ፡ ራሱን ፡ የሚያጐላ አባብሎ ፡ ወሰደን ፡ ሆነናል ፡ ተላላ አዝ፦ አቤቱ ፡ ሕዝብህን ፡ መልሰን ሳንጠፋ ፡ ቀድመህ ፡ ድረስልን አቤቱ ፡ ልጆችህን ፡ አስበን ከድፍረት ፡ ከውድቀት ፡ ታደገን በጐ ፡ በሚመስል ፡ ሃሳብ ፡ እየተሳበ በመልካም ፡ ንግግር ፡ ሕዝብ ፡ ተሰበሰበ ዓመጸ ፡ ማይከለክል ፡ የረሳ ፡ ፍርድህን እራሳችንን ፡ እንዳናይ ፡ አደንዝዞ ፡ አሰረን በዘመን ፡ ፍጻሜ ፡ ጫፍ ፡ ላይ ፡ ሆነን ፡ ሳለን ልባችን ፡ እንዳያይ ፡ ምንው ፡ ተደለለ ዘይታችንን ፡ እንሙላ ፡ ጊዜው ፡ ሳይገባደድ ፈጥነን ፡ እንመለስ ፡ ከሄድንበት ፡ መንገድ አዝ፦ አቤቱ ፡ ሕዝብህን ፡ መልሰን ሳንጠፋ ፡ ቀድመህ ፡ ድረስልን አቤቱ ፡ ልጆችህን ፡ አስበን ከድፍረት ፡ ከውድቀት ፡ ታደገን