Loading
Singer
Updated 8/31/2026
በዙፋኑ ፡ ላይም ፡ በተቀመጠው ፡ በቀኝ ፡ እጁ ፡ ላይ ፡ በውስጥና ፡ በኋላ ፡ የተጻፈበት በሰባትም ፡ ማኅተም ፡ የተዘጋ ፡ መጽሃፍ ፡ አየሁ ። ብርቱም ፡ መልአክ ፡ "መጽሃፉን ፡ ይዘረጋ ፡ ዘንድ ፤ ማኅተሞቹንም ፡ ይፈታ ፡ ዘንድ ፡ የሚገባው ፡ ማነው?" ፡ ብሎ ፡ በታላቅ ፡ ድምጽ ፡ ሲያውጅ ፡ አየሁ ። በሰማይም ፡ ቢሆን ፤ በምድርም ፡ ቢሆን ፤ ከምድርም ፡ በታች ፡ ቢሆን ፤ መጽሃፉን ፡ ሊዘረጋ ፡ ወይም ፡ ሊመለከተው ፡ ማንም ፡ አልተቻለውም ። መጽሃፉንም ፡ ሊዘረጋ ፡ ወይም ፡ ሊመለከተው ፡ የሚገባው ፡ ማንም ፡ ስላልነበረ ፡ እጅግ ፡ አለቀስኩ ። ከሽማግሌዎቹም ፡ አንዱ "አታልቅስ ፡ እነሆ ፡ ከይሁዳ ፡ ነገድ ፡ የሆነው ፡ አንበሳ ፡ እርሱም ፡ የዳዊት ፡ ስር ፡ መጽሃፉን ፡ ይዘረጋ ፡ ዘንድ ፡ ሰባቱንም ፡ ማኅተም ፡ ይፈታ ፡ ዘንድ ፡ ድል ፡ ነስቷል" ፡ አለኝ ። [1] መልአክት ፡ አዲስ ፡ ቅኔ ፡ ይዘምራሉ እንዲህ ፡ እያሉ ፡ መጽሃፍት ፡ ወስደን ማኅተሞቹን ፡ ትፈታ ፡ ዘንድ ፡ ይገባሃል ይገባሃል (፫x) ፡ ታርደሃልና ፡ ትፈታ ፡ ዘንድ ፡ ይገባሃል ሌሎች ፡ ሲሉ ፡ ሰማሁ ፡ የታረደው ፡ በግ ሃይልና ፡ ባለጠግነት ፣ ጥበብ ፡ ብርታት ፣ ክብር ፡ ምሥጋና ፡ በረከት ይቀበል ዘንድ ፡ ይገባዋል (፪x) ፡ በረከትን ፡ ይቀበል ፡ ዘንድ ፡ ይገባዋል በረከት ፡ እና ፡ ክብር ፡ ምሥጋና ፡ ሃይልም ከዘለዓለም ፡ እስከዘለዓለም ፡ በዙፋኑ ፡ ላይ ፡ ለተቀመጠው ፡ በጉ ፡ ይሁን ደግሞ ፡ እያሉት ፡ ቅዱሳኑ ፡ ለበጉ ፡ ክብር ይቀኛሉ ፡ ይዘምራሉ ፡ ያዜማሉ