Loading
Singer
ምክርህ ፡ ሲሰራ ፡ አይቼ ፡ ተደስቻለሁ ማይከለከል ፡ ሃሳብህ ፡ አውቄዋለሁ ድንቅህን ፡ አይቼ ፡ ብገረም ፡ ቆምኩኝ ፡ ላመልክህ በሰው ፡ ሁሉ ፡ ፊት ፡ ተገልጧል ፡ አደራረግህ አዝ፦ ተባረክ ፡ ከዚህ ፡ ሌላ ፡ ምን ፡ እላለሁ ጌታዬ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ አውቄያለሁ ዘመኔን ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ እንድኖር ፡ ጌታ በቃልህ/በምክርህ ፡ ደገፍከኝ ፡ እንዳልረታ (፪x) አንተን ፡ አምኜ ፡ ወደፊት ፡ እራመዳለሁ ወሬ ፡ ሰምቼ ፡ ኋላዬን ፡ መቼ ፡ አያለሁ ዘለዓለሜ ፡ በእጅህ ፡ ነው ፡ ልቤ ፡ እንዳይሰጋ የምታመንህ ፡ ጌታዬ ፡ አለህ ፡ ከእኔ ፡ ጋር አዝ፦ ተባረክ ፡ ከዚህ ፡ ሌላ ፡ ምን ፡ እላለሁ ጌታዬ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ አውቄያለሁ ዘመኔን ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ እንድኖር ፡ ጌታ በቃልህ/በምክርህ ፡ ደገፍከኝ ፡ እንዳልረታ (፪x) የሰው ፡ ዓይን ፡ የለህ ፡ እንደሰው ፡ መቼ ፡ ታያለህ ጆሮህስ ፡ እንደሰማቸው ፡ መች ፡ ትፈርዳለህ መንገዱ ፡ ይሄ ፡ ነው ፡ ብሎ ፡ ሚመራህ ፡ የለም በምክርህ ፡ ግሩም ፡ ትክክል ፡ ጻድቅ ፡ አምላክ ፡ ነህ አዝ፦ ተባረክ ፡ ከዚህ ፡ ሌላ ፡ ምን ፡ እላለሁ ጌታዬ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ አውቄያለሁ ዘመኔን ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ እንድኖር ፡ ጌታ በቃልህ/በምክርህ ፡ ደገፍከኝ ፡ እንዳልረታ (፪x) ለዘሪ ፡ ዘርን ፡ የምትሰጥ ፡ ፍሬ ፡ እንዲበላ ከሕይወት ፡ እንዳይጐድል ፡ ሞቶ ፡ የኋላ ፡ ኋላ ለእኔም ፡ ቃልህን ፡ ሰጥተኸኛል ፡ ምን ፡ አስባለሁ ተስፋ ፡ ቢስ ፡ ሆኜ ፡ አልቀረሁም ፡ አከብርሃለሁ አዝ፦ ተባረክ ፡ ከዚህ ፡ ሌላ ፡ ምን ፡ እላለሁ ጌታዬ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ አውቄያለሁ ዘመኔን ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ እንድኖር ፡ ጌታ በቃልህ/በምክርህ ፡ ደገፍከኝ ፡ እንዳልረታ (፪x)