Loading
Singer
ከጉብዝናህ ፡ ሚስትህ ፡ ጋር ፡ ደስ ፡ ይበልህ ፡ አዎ ፡ ደስ ፡ ይበልህ ውደዳት ፡ አፍቅራት ፡ እርሷን ፡ እንደራስህ እህትህም ፡ ሚስትህም ፡ ባልንጀራህም ፡ ነች እረዳትህ ፡ ሆና ፡ ለአንተ ፡ የተሰጠች (፪x) በረከት ፡ ካገኘ ፡ ሚስትን ፡ ያገኘ ፡ ሰው ከእግዚአብሔርም ፡ ዘንድ ፡ ሞገስ ፡ ከተሰጠ እያመሰገነ ፡ ስለዚህ ፡ ስጦታ ቤቱን ፡ በጽድቅ ፡ ይምራ ፡ ይንከባከባታል (፪x) አዝ፦ የቃልኪዳን ፡ ተጋቢዎች ፡ እናንተን ፡ ያጣመረ በመሃከላቹህ ፡ እግዚአብሔር ፡ አለ በመሃከላቹህ ፡ እግዚአብሔር ፡ አለ በመሃከላቹህ ፡ ምስክር ፡ እርሱ ፡ አለ በመሃከላቹህ ፡ ምስክር ፡ እርሱ ፡ አለ (፪x) እድምተኛ ፡ አይደለም ፡ በልቶና ፡ ጠጥቶ እንደሚሸኝ ፡ ወዳጅ ፡ ለእናንተው ፡ ትቶ ያስጀመረ ፡ ጌታ ፡ አብሯቹህ ፡ ይዘልቃል ብቻ ፡ አባት ፡ ሆይ ፡ በሉት ፡ ቤቱ ፡ ቤት ፡ ይሆናል (፪x) አስተዋይ ፡ ሚስት ፡ ግን ፡ ከእግዚአብሔር ፡ ዘንድ ፡ ናት በእግዚአብሔር ፡ ቃል ፡ ላይ ፡ እንደተባለላት ለጌታ ፡ ለኢየሱስ ፡ እንደምትገዢ ለባልሽም ፡ ደግሞ ፡ እንዲሁ ፡ ተገዢ (፪x) ልባም ፡ ሴት ፡ ለባሏ ፡ ዘውድ ፡ እንደምትሆነው ክብሩ ፡ የት ፡ እንዳለ ፡ ቃሉ ፡ ካጸደቀው ማፈሪያህ ፡ እንዳይሆን ፡ አንቺም ፡ እንዲህ ፡ ሁኚ ግን ፡ ልባምነትን ፡ ከቃሉ ፡ አግኚ (፪x) አዝ፦ የቃልኪዳን ፡ ተጋቢዎች ፡ እናንተን ፡ ያጣመረ በመሃከላቹህ ፡ እግዚአብሔር ፡ አለ በመሃከላቹህ ፡ እግዚአብሔር ፡ አለ በመሃከላቹህ ፡ ምስክር ፡ እርሱ ፡ አለ በመሃከላቹህ ፡ ምስክር ፡ እርሱ ፡ አለ (፪x) እድምተኛ ፡ አይደለም ፡ በልቶና ፡ ጠጥቶ እንደሚሸኝ ፡ ወዳጅ ፡ ለእናንተው ፡ ትቶ ያስጀመረ ፡ ጌታ ፡ አብሯቹህ ፡ ይዘልቃል ብቻ ፡ አባት ፡ ሆይ ፡ በሉት ፡ ቤቱ ፡ ቤት ፡ ይሆናል (፪x) የብልህ ፡ ቤት ፡ ይሁን ፡ ክርስቶስ ፡ ራስ ፡ ሆኖ ዐይንም ፡ በእርሱ ፡ አድርጐ ፡ በስሙ ፡ ተማምኖ መንገዱን ፡ ዝለቁት ፡ የኑሮን ፡ ጐዳና ግልጽ ፡ ሁኑ ፡ ሁሉን ፡ ነገር ፡ ተከባበሩና (፪x) ዕውቀትን ፡ እንደዘውድ ፡ በላያቹህ ፡ ጫኑ ጥበብን ፡ እንዳትዉ ፡ ሞኞች ፡ እንዳትሆኑ በፍቅር ፡ ለጸና ፡ ለተቻቻለ ፡ ሰው ጋብቻ ፡ ክቡር ፡ ነው ፡ መኝታው ፡ ንጹህ ፡ ነው (፪x) አዝ፦ የቃልኪዳን ፡ ተጋቢዎች ፡ እናንተን ፡ ያጣመረ በመሃከላቹህ ፡ እግዚአብሔር ፡ አለ በመሃከላቹህ ፡ እግዚአብሔር ፡ አለ በመሃከላቹህ ፡ ምስክር ፡ እርሱ ፡ አለ በመሃከላቹህ ፡ ምስክር ፡ እርሱ ፡ አለ (፪x) እድምተኛ ፡ አይደለም ፡ በልቶና ፡ ጠጥቶ እንደሚሸኝ ፡ ወዳጅ ፡ ለእናንተው ፡ ትቶ ያስጀመረ ፡ ጌታ ፡ አብሯቹህ ፡ ይዘልቃል ብቻ ፡ አባት ፡ ሆይ ፡ በሉት ፡ ቤቱ ፡ ቤት ፡ ይሆናል (፪x) እግዚአብሔር ፡ አለ (፬x) ፤ እግዚአብሔር ፡ አለ (፬x) እግዚአብሔር ፡ አለ (፬x) ፤ እግዚአብሔር ፡ አለ (፬x) እግዚአብሔር ፡ አለ (፬x) ፤ እግዚአብሔር ፡ አለ (፬x) እግዚአብሔር ፡ አለ (፬x)