Loading
Singer
መክበሬ ፡ በአንተ ፡ ነው ፡ እንዲህ ፡ መዘመሬ ከፍታ ፡ ላይ ፡ ወጣሁ ፡ ጸንቶ ፡ ቆሟል ፡ እግሬ (፪x) ቅባቱን ፡ ለቆብኝ ፡ በእኔ ፡ ከከበረ ገና ፡ እዘምራለሁ ፡ ጠላቴ ፡ ሆይ ፡ ስማ ቅባቱ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ አለው ፡ ልዩ ፡ አላማ (፪x) አለው ፡ ልዩ ፡ አላማ (፪x) አዝ፦ አቤት (፫x) ፡ አቤት (፪x) የአምላኬ ፡ ድንቅ ፡ ስራው ይገርመኛል ፡ ይደንቀኛል እንዲህ ፡ ማክበሩ ፡ ይገርመኛል ማሳመሩ ፡ ይደንቀኛል እኔን ፡ መምረጡ ፡ ይገርመኛል ሰው ፡ ማድረጉ ፡ ይገርመኛል ታናሽነቴን ፡ አይተህ ፡ ሳትንቀኝ ከማህጸን ፡ ሳልወጣ ፡ አንተ ፡ የለየኸኝ ፡ ጌታ ፡ የለየኸኝ ገሃድ ፡ አወጣኸኝ ፡ ነገር ፡ አለ ፡ በእኔ ይገለጥ ፡ ክብርህ ፡ ቅባቱ ፡ ይጨምር የምትሰራው ፡ በእኔ (፪x) የምትሰራው ፡ በእኔ (፪x) አዝ፦ አቤት (፫x) ፡ አቤት (፪x) የአምላኬ ፡ ድንቅ ፡ ስራው ይገርመኛል ፡ ይደንቀኛል እንዲህ ፡ ማክበሩ ፡ ይገርመኛል ማሳመሩ ፡ ይደንቀኛል እኔን ፡ መምረጡ ፡ ይገርመኛል ሰው ፡ ማድረጉ ፡ ይገርመኛል አንተ ፡ ከመረጥከኝ ፡ ልጅህ ፡ ካደረከኝ በሰጠኸኝ ፡ ፀጋ ፡ ታማኝ ፡ ሰው ፡ አድርገኝ (፪x) ይህ ፡ ገና ፡ ጅምር ፡ ነው ፡ አለ ፡ ገና ፡ ገና እወርሳለሁ (፪x) ፡ እወርሳለሁ ፡ ገና (፪x) እወርሳለሁ ፡ ገና (፪x) አዝ፦ አቤት (፫x) ፡ አቤት (፪x) የአምላኬ ፡ ድንቅ ፡ ስራው ይገርመኛል ፡ ይደንቀኛል እንዲህ ፡ ማክበሩ ፡ ይገርመኛል ማሳመሩ ፡ ይደንቀኛል እኔን ፡ መምረጡ ፡ ይገርመኛል ሰው ፡ ማድረጉ ፡ ይገርመኛል