Loading
Singer
የጌታን ፡ ቸርነት ፡ ምህረቱን ፡ ሳስበው መውጣቴ ፡ መግባቴ ፡ መኖሬ ፡ በእርሱ ፡ ነው ለእኔ ፡ የበዛው ፡ ፍቅር ፡ እጅግ ፡ ይገርመኛል ሁሌ ፡ ሳታቋርጥ ፡ አመስግን ፡ ይለኛል እጆቼን ፡ ወደ ፡ ጌታ ፡ ወደ ፡ ኢየሱስ ፡ ዘርግቼ አመሰግነዋለሁ ፡ ስለተዋቡት ፡ ቀኖቼ ኢየሱስ ፡ ሕያው ፡ አለት ፡ የኔ ፡ ጽኑ ፡ መሰረት ምሥጋና ፡ ይብዛህ ፡ እንጂ ፡ ምሥጋና ፡ አይነስበት አዝ:- ምህረቱን ፡ አይቼ ፡ ነው ፡ ፍቅሩን ፡ ቀምሼ ፡ ነው ዛሬ ፡ ደስ ፡ ብሎኝ ፡ በፊቱ ፡ ቆሜ ፡ ምዘምረው (፪x) በአባትነት ፡ ፍቅሩ ፡ ሁሌ ፡ እየመከረኝ እግሬ ፡ ሲንሸራተት ፡ ይዞ ፡ እየደገፈኝ በጸጋው ፡ ከልሎ ፡ እዚህ ፡ አድርሶኛል እንዳመሰግነው ፡ ውስጤ ፡ ግድ ፡ ይለኛል ልዘምር ፡ ለጌታዬ ፡ እርሱ ፡ ምሥጋናዬ ፡ ነው እግሬን ፡ እመሰናከል ፡ ነፍሴ ፡ ከሞት ፡ ላዳነው ልቅረብ ፡ በፊቱ ፡ ልስገድ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ወዶኛል ሁልጊዜ ፡ ጠዋት ፡ አማታ ፡ ሳመልከው ፡ ደስ ፡ ይለኛል አዝ:- ምህረቱን ፡ አይቼ ፡ ነው ፡ ፍቅሩን ፡ ቀምሼ ፡ ነው ዛሬ ፡ ደስ ፡ ብሎኝ ፡ በፊቱ ፡ ቆሜ ፡ ምዘምረው (፪x) ተአምራቱን ፡ ያየ ፡ ፍቅር ፡ የበዛለት ድንቁ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ሞገስ ፡ የሆነለት ሳይቆጥብ ፡ ይናገር ፡ ያውራ ፡ የእርሱን ፡ ስራ ተአምር ፡ እንደሚያድርግ ፡ ድንቅን ፡ እንደሚሰራ ይናገር ፡ የቀመሰ ፡ ፍቅሩን ፡ መልካምነቱን የሚያድን ፡ የሚታደግ ፡ ብሩህ ፡ አባት ፡ መሆኑን አምላክ ፡ ነው ፡ የሚያስመካ ፡ እረዳት ፡ ድንቅ ፡ ሰሪ ዘመኑ ፡ ቁጥር ፡ የለው ፡ ጌታ ፡ ዘለዓለም ፡ ነዋሪ አዝ:- ምህረቱን ፡ አይቼ ፡ ነው ፡ ፍቅሩን ፡ ቀምሼ ፡ ነው ዛሬ ፡ ደስ ፡ ብሎኝ ፡ በፊቱ ፡ ቆሜ ፡ ምዘምረው (፪x)