Loading
Singer
በመንገድህ ፡ አግኘኝ ፡ ጌታ ፡ እንደ ፡ ሀሳብህ ለትጐበኘኝ ፡ ስትመጣ ፡ እንዳልጠፋ ፡ ከፊትህ ፀጋህን ፡ አብዛልኝ ፡ ኢየሱስ ፡ በሕይወቴ መንፈስህ ፡ ያግዘኝ ፡ ይጽና ፡ መሰረቴ (፪x) አዝ፦ ምህረትን ፡ ትወዳለህና ብርታትን ፡ ትሰጣለህና እኔም ፡ ልታሰብ ፡ ጌታ ኃይል ፡ ይብዛልኝ ፡ ልበርታ ኑሮዬ ፡ አንተን ፡ ይምሰልህ ከፍ ፡ ያድርግህ ፡ ያክብርህ ፡ አሜን ስለ ፡ እኔ ፡ ነፍስህን ፡ ልትሰጥ ፡ አልሰሰትክምና እዳዬን ፡ ሁሉ ፡ ልትከፍል ፡ ተችሎሀልና እኔም ፡ ለመውደድህ ፡ ልሁን ፡ እንደልብህ አንተን ፡ መፍራት ፡ ሙላኝ ፡ ዝቅ ፡ ልበልልህ (፪x) አዝ፦ ምህረትን ፡ ትወዳለህና ብርታትን ፡ ትሰጣለህና እኔም ፡ ልታሰብ ፡ ጌታ ኃይል ፡ ይብዛልኝ ፡ ልበርታ ኑሮዬ ፡ አንተን ፡ ይምሰልህ ከፍ ፡ ያድርግህ ፡ ያክብርህ ፡ አሜን በመቅደስህ ፡ ቀድሰኝ ፡ በእሣትህ ፡ አንጥረኝ የማትወደው ፡ ከእኔ ፡ ይቆረጥ ፡ እንዳሻህ ፡ አበጃጀኝ ለእኔም ፡ የሻለኛል ፡ በእጅህ ፡ መቀረፁ ኋላ ፡ ሞልቶ ፡ ይፈሣል ፡ ከአንተ ፡ በረከቱ (፪x) አዝ፦ ምህረትን ፡ ትወዳለህና ብርታትን ፡ ትሰጣለህና እኔም ፡ ልታሰብ ፡ ጌታ ኃይል ፡ ይብዛልኝ ፡ ልበርታ ኑሮዬ ፡ አንተን ፡ ይምሰልህ ከፍ ፡ ያድርግህ ፡ ያክብርህ ፡ አሜን ድንጋዩ ፡ ልብ ፡ ከእኔ ፡ ይውጣ ፡ ስጋ ፡ ይሁንልኝ የቀናውን ፡ መንፈስህን ፡ በውስጤ ፡ አድስልኝ ክርስቲያን ፡ ከተባልኩ ፡ በአንተ ፡ ከተጠራሁ እንደ ፡ ሀሳብህ ፡ ኖሬ ፡ ማለፍን ፡ እሻለሁ (፪x) አዝ፦ ምህረትን ፡ ትወዳለህና ብርታትን ፡ ትሰጣለህና እኔም ፡ ልታሰብ ፡ ጌታ ኃይል ፡ ይብዛልኝ ፡ ልበርታ ኑሮዬ ፡ አንተን ፡ ይምሰልህ ከፍ ፡ ያድርግህ ፡ ያክብርህ ፡ አሜን (፪x)