Loading
Singer
አዝ፦ ውዴ (፫x) ፡ ኢየሱስ (፫x) ምህረትህን ፡ አይቻለሁ ፡ አወራለሁ ምሕረትህን ፡ አይቻለሁ ፡ ዘምራለሁ ማዳንህን ፡ ቀምሻለሁ ፡ አወራለሁ ማዳንህን ፡ ቀምሻለሁ ፡ ዘምራለሁ (፪x) አስራ ፡ ሁለት ፡ ዓመት ፡ ደም ፡ እየፈሰሰኝ ተነጥዬ ፡ መኖር ፡ ሰው ፡ እንኳን ፡ እራቀኝ ከእንግዲህስ ፡ ወዲያ ፡ ተስፋዬ ፡ ምንድን ፡ ነው ዕድሜዬ ፡ በሙሉ ፡ በለቅሶ ፡ ሊያልቅ ፡ ነው ብዬ ፡ ደምድሜ ፡ ሃሳቤን ፡ ስጠብቀው ፡ ፍጻሚዬን ድንገት: ብርሃን: ወጣልኝ: አዳኜ ፡ ኢየሱስ ፡ መጣልኝ አዝ፦ ውዴ (፫x) ፡ ኢየሱስ (፫x) ምህረትህን ፡ አይቻለሁ ፡ አወራለሁ ምሕረትህን ፡ አይቻለሁ ፡ ዘምራለሁ ማዳንህን ፡ ቀምሻለሁ ፡ አወራለሁ ማዳንህን ፡ ቀምሻለሁ ፡ ዘምራለሁ ግርግሩ ፡ በዝቶ ፡ የሚጋፋው ፡ ሰው አዳኜ ፡ ኢየሱስን ፡ እንዴት ፡ ላግኘው ተስፋ ፡ ባለመቁረጥ ፡ እየተንፉቀኩኝ እጄን ፡ ሰደድኩና ፡ ቀሚሱን ፡ ነካሁኝ ነካ ፡ ባደርገው ፡ ነካኝ ፡ ኃይልም ፡ ወጣና ፡ ዳንኩኝ ታዲያ ፡ ምን ፡ ልበል ፡ ይህን ፡ ጌታ ፡ አመስግኑልኝ ፡ በልልታ አዝ፦ ውዴ (፫x) ፡ ኢየሱስ (፫x) ምህረትህን ፡ አይቻለሁ ፡ አወራለሁ ምሕረትህን ፡ አይቻለሁ ፡ ዘምራለሁ ማዳንህን ፡ ቀምሻለሁ ፡ አወራለሁ ማዳንህን ፡ ቀምሻለሁ ፡ ዘምራለሁ ዘመናት ፡ አለፉ ፡ ሆኜ ፡ በጭንቀት ለደሜ ፡ ማድረቂያ ፡ ጠፍቶ ፡ መድሐኒት ማንም ፡ ማይጠጋኝ ፡ እርኩስ: ናት: ተብዬ አሁንስ ፡ መረረኝ ፡ ገላግለኝ ፡ ጌታዬ ብዬ ፡ ሞቴንም ፡ ስናፍቅ ፡ በሽታዬ: አርጎኝ: ድቅቅ መሲሁ ፡ መጣልኝና ፡ አቆመኝ ፡ ፈወሰኝና አዝ፦ ውዴ (፫x) ፡ ኢየሱስ (፫x) ምህረትህን ፡ አይቻለሁ ፡ አወራለሁ ምሕረትህን ፡ አይቻለሁ ፡ ዘምራለሁ ማዳንህን ፡ ቀምሻለሁ ፡ አወራለሁ ማዳንህን ፡ ቀምሻለሁ ፡ ዘምራለሁ ትድናለች ፡ ብሎ ፡ ኧረ ፡ ማን ፡ ገመተኝ ሁሉም ፡ በሩቅ ፡ ሲሸሽ፡ ጀርባውን ፡ ሲሰጠኝ አስታማሚ ፡ አጥቼ ፡ የምደግፈኝ ኢየሱስ ፡ ሲጐበኘኝ ፡ በዛ ፡ ሚያጅበኝ የሸሹኝ ፡ ሁሉ ፡ አቀፉኝ፡ የናቁኝ ፡ ሁሉ ፡ አከበሩኝ መሸማቀቄም ፡ ቀረልኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ይመስገንልኝ አዝ፦ ውዴ (፫x) ፡ ኢየሱስ (፫x) ምህረትህን ፡ አይቻለሁ ፡ አወራለሁ ምሕረትህን ፡ አይቻለሁ ፡ ዘምራለሁ ማዳንህን ፡ ቀምሻለሁ ፡ አወራለሁ ማዳንህን ፡ ቀምሻለሁ ፡ ዘምራለሁ