Loading
Singer
እየመሽ ፡ ነጋ ፡ እየነጋም ፡ መሽ ዛሬም ፡ ጉስቁልና ፡ ከምድሪቱ ፡ እልሸሸ ሁካቴ ፡ የፀናበት ፡ የአልጋ ፡ ቁራኛ ፡ ሰው ታሞ ፡ ማያገግም ፡ ማቁን ፡ አለበሰው ቀባሪ ፡ ደከመው ፡ ግራ ፡ ቅኝ ፡ እሬሳ ሃዘን ፡ ተቀማጩም ፡ ዛሬም ፡ አልተነሳ ጥቁር ፡ የለበሰ ፡ የተላጨ ፡ ፀጉሩ ወዳጁን ፡ ያጣ ፡ ሰው ፡ ፈሷል ፡ በመንደሩ ፡ አሂሂ ፡ ፈሷል ፡ በመንደሩ ዛሬም ፡ ገና ፡ ነው ገና ፡ ነው ፡ ምህረቱ ፡ አልወረደም የሃገሬ ፡ ንዳድ ፡ ዛሬም ፡ አልበረደም ፡ አዎ ፡ ገና ፡ ነው ፡ ቁጣው ፡ መቸ ፡ ሰከነ በሽታና ፡ ርሃብ ፡ ባገሬ ፡ በወንዜ፡ ገነነ ከማዶ ፡ ይሰማል ፡ እሪታ ፡ ከሩቅ የሞት ፡ ልጆች ፡ ለቅሶ ፡ ዋይታ ፡ የሚሰቅቅ አፅናኝ ፡ ሆይ ፡ ውረድ ፡ ወደ ፡ ምድር ምሕረትህ ፡ ይጐብኘን ፡ ይውደቅ ፡ የሞት ፡ በትር አፅናኝ ፡ ሆይ ማረን ፡ ጌታችን ፡ ፈጽመህ ፡ አትቅጣን ጠበልክን ፡ እርጨን ፡ ጠምቶናል ፡ አጠጣን ታማሚው ፡ ይፈወስ ፡ የራበው ፡ ሰው ፡ ይጥገብ የፍርድ ፡ አዋጅ ፡ በቅቶ ፡ ምህረቱ ፡ ይነበብ ከትናንት ፡ ዛሬ ፡ ይሻል ፡ ይሆን ፡ ብለን የበጐ ፡ ቀን ፡ ያለህ ፡ አልመጣም ፡ ጠብቀን የነገዋ ፡ ፀሐይ ፡ ሙቀት ፡ ይዛ ፡ ትምጣ የሃገር ፡ ልጅ ፡ በርዶታል ፡ ድሪቶም ፡ ስላጣ በረሃብ ፡ ጉስቁልና ፡ በጥማት ፡ ተቃጥሎ በብርድ ፡ ተጠብሶ ፡ በፀሐይ ፡ ከሳስሎ ኑሮ ፡ እንደሬት ፡ መሮት ፡ ለሞቱ ፡ የሚጐመጅ በጐዳናው ፡ ከፈፍ ፡ ተዘርግቷል ፡ እድጅ ፡ አሂሂ ፡ ተዘርግቷል ፡ እደጅ ዛሬም ፡ ገና ፡ ነው ገና ፡ ነው ፡ ምህረቱ ፡ አልወረደም የሃገሬ ፡ ንዳድ ፡ ዛሬም ፡ አልበረደም ፡ አዎ ፡ ገና ፡ ነው ፡ ቁጣው ፡ መቸ ፡ ሰከነ በሽታና ፡ ርሃብ ፡ ባገሬ ፡ በወንዜ፡ ገነነ ከማዶ ፡ ይሰማል ፡ እሪታ ፡ ከሩቅ የሞት ፡ ልጆች ፡ ለቅሶ ፡ ዋይታ ፡ የሚሰቅቅ አፅናኝ ፡ ሆይ ፡ ውረድ ፡ ወደ ፡ ምድር ምሕረትህ ፡ ይጐብኘን ፡ ይውደቅ ፡ የሞት ፡ በትር አፅናኝ ፡ ሆይ ማረን ፡ ጌታችን ፡ ፈጽመህ ፡ አትቅጣን ጠበልክን ፡ እርጨን ፡ ጠምቶናል ፡ አጠጣን ታማሚው ፡ ይፈወስ ፡ የራበው ፡ ሰው ፡ ይጥገብ የፍርድ ፡ አዋጅ ፡ በቅቶ ፡ ምህረቱ ፡ ይነበብ ክራራይሶ (፪x) ፡ እግዚኦ ፡ ማሃረነ ፡ ክርስቶስ (፪x)