Loading
Singer
አዝ፦ መገረም ፡ ገብቶበት ፡ ቃል ፡ እንደጠፋዉ የልቤን ፡ ለመግለጽ ፡ ቋንቋ ፡ እንዳጠረዉ በአሰራርህ ፡ ነፍሴ ፡ ተደንቃ ፡ ኖራለች ምሥጋናው ፡ አንሶባት ፡ እንባን ፡ ታፈሳለች ተባረክ ፡ ትልሃለች ተመስገን ፡ ትልሃለች ከፍ ፡ በል ፡ ትልሃለች ነፍሴ ፡ እጅግ ፡ ወዳሃለች (፪x) ከገመትኩትና ፡ ካሰብኩት ፡ በላይ ማዳንህ ፡ ሲገለጥ ፡ ከላይ ፡ ከሰማይ ሲደራረብብኝ ፡ ቸርነት ፡ ምህረትህ የምለው ፡ ሲጠፋኝ ፡ አምላኬ ፡ በፊትህ እንባ ፡ ቋንቋዬ ነው ፡ ይፍሰስ ፡ ከእግርህ ፡ ሥር ያለኝን ፡ ምሥጋና ፡ ያውጣው ፡ ይናገር ይገባሃልና ፡ የነፍሴ ፡ ስሜቷ ባክህ ፡ ዝም ፡ አትበል ፡ ተቀበላት ፡ ጌታ አዝ፦ መገረም ፡ ገብቶበት ፡ ቃል ፡ እንደጠፋዉ የልቤን ፡ ለመግለጽ ፡ ቋንቋ ፡ እንዳጠረው በአሰራርህ ፡ ነፍሴ ፡ ተደንቃ ፡ ኖራለች ምሥጋናው ፡ አንሶባት ፡ እንባን ፡ ታፈሳለች ተባረክ ፡ ትልሃለች ተመስገን ፡ ትልሃለች ከፍ ፡ በል ፡ ትልሃለች ነፍሴ ፡ እጅግ ፡ ወዳሃለች (፪x) እንዲሁ ፡ ተመስገን ፡ ብዬ ፡ የማላልፈው ደግሞም ፡ በቋንቋዬ ፡ በቃል ፡ የማልገልጸው በዘመኔ ፡ ሁሉ ፡ ከቶ ፡ ማልረሳው አምላክ ፡ ቸርነትህ ፡ ለኔስ ፡ ብዙ ፡ ነው አቤት ፡ አሰራርህ ፡ እጅግ ፡ ይደንቀኛል መናገር ፡ ስጀምር ፡ እንባ ፡ ይቀድመኛል ለማመስገን ፡ ቋንቋ ፡ ቃል ፡ አጥሮኛልና በእንባዬ ፡ ላክብርህ ፡ ልውደቅ ፡ ልስገድና አዝ፦ መገረም ፡ ገብቶበት ፡ ቃል ፡ እንደጠፋዉ የልቤን ፡ ለመግለጽ ፡ ቋንቋ ፡ እንዳጠረው በአሰራርህ ፡ ነፍሴ ፡ ተደንቃ ፡ ኖራለች ምሥጋናው ፡ አንሶባት ፡ እንባን ፡ ታፈሳለች ተባረክ ፡ ትልሃለች ተመስገን ፡ ትልሃለች ከፍ ፡ በል ፡ ትልሃለች ነፍሴ ፡ እጅግ ፡ ወዳሃለች (፪x) እግዚአብሔር ፡ አምላኬ ፡ ሆንከኝ ፡ ደስ ፡ ብሎኛል ከዚህ ፡ በላይ ፡ ባርኮት ፡ ከቶ ፡ የት ፡ ይገኛል አንተን ፡ ያገኘሁ ፡ ቀን ፡ ቤት ፡ ኑሮዬ ፡ ሞላ ለዘመኔ ፡ ሁሉ ፡ ተገኘለት ፡ መላ ምላሽ ፡ ባይሆነኝም ፡ ይህ ፡ የኔ ፡ ምሥጋና ላደርግ ፡ የምችለው ፡ ይሄንን ፡ ነውና ስለዚህ ፡ ተባረክ ፡ እላለሁ ፡ ከነፍሴ የምወድህ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ንጉሤ አዝ፦ መገረም ፡ ገብቶበት ፡ ቃል ፡ እንደጠፋዉ የልቤን ፡ ለመግለጽ ፡ ቋንቋ ፡ እንዳጠረው በአሰራርህ ፡ ነፍሴ ፡ ተደንቃ ፡ ኖራለች ምሥጋናው ፡ አንሶባት ፡ እንባን ፡ ታፈሳለች ተባረክ ፡ ትልሃለች ተመስገን ፡ ትልሃለች ከፍ ፡ በል ፡ ትልሃለች ነፍሴ ፡ እጅግ ፡ ወዳሃለች (፪x)