Loading
Singer
አዝ፦ ነገር ፡ ግን ፡ መንገዴን ፡ በፊቱ ፡ አጸናለሁ ቢገድለኝም ፡ እንኳን ፡ እርሱን ፡ ጠብቃለሁ እርሱን ፡ ጠብቃለሁ ፡ ጠብቃለሁ ፡ ጠብቃለሁ (፪x) የሆነው ፡ ነገር ፡ ይምጣብኝ ፡ ሥጋዬን ፡ በጥርሴ ፡ እይዛለሁ ቢገድለኝ ፡ እንኳን ፡ ታግሼ ፡ ሕይወቴን ፡ በእጁ ፡ አኖራለሁ መድሃኒት ፡ ይሆንልኛል ፡ ነገሩ ፡ አይመረመርም እጠብቀዋለሁ ፡ ጌታን ፡ በጥቂቱ ፡ ዝዬ ፡ አልወድቅም አዝ፦ ነገር ፡ ግን ፡ መንገዴን ፡ በፊቱ ፡ አጸናለሁ ቢገድለኝም ፡ እንኳን ፡ እርሱን ፡ ጠብቃለሁ እርሱን ፡ ጠብቃለሁ ፡ ጠብቃለሁ ፡ ጠብቃለሁ (፪x) በለስ ፡ እንኳን ፡ ባታፈራ ፡ የወይን ፡ ሃረግ ፡ ቢደርቅ ዝም ፡ ብዬ ፡ የጌታን ፡ ቀን ፡ በትዕግሥት ፡ ልጠብቅ የወራት ፡ ስራ ፡ ቢጐድል ፡ እርሾቼም ፡ ባያበሉኝ እግዚአብሔር ፡ ኃይሌ ፡ ይሆናል ፡ ጥሩ ፡ ሰዓት ፡ ሲወጣልኝ አዝ፦ ነገር ፡ ግን ፡ መንገዴን ፡ በፊቱ ፡ አጸናለሁ ቢገድለኝም ፡ እንኳን ፡ እርሱን ፡ ጠብቃለሁ እርሱን ፡ ጠብቃለሁ ፡ ጠብቃለሁ ፡ ጠብቃለሁ (፪x) በውስጤ ፡ ስላደረው ፡ ተስፋ ፡ መንፈሱ ፡ አያሳፍረኝም እንደ ፡ ኢዮብ ፡ ሳያጽናናኝ ፡ እግዚአብሔር ፡ ከቶ ፡ አይተወኝም ከጋጣዬ ፡ የጠፉት ፡ ላሞች ፡ ነገ ፡ ይበራከታሉ ያላገጡብኝ ፡ ጠላቶች ፡ የአምላኬን ፡ ስራ ፡ ያያሉ አዝ፦ ነገር ፡ ግን ፡ መንገዴን ፡ በፊቱ ፡ አጸናለሁ ቢገድለኝም ፡ እንኳን ፡ እርሱን ፡ ጠብቃለሁ እርሱን ፡ ጠብቃለሁ ፡ ጠብቃለሁ ፡ ጠብቃለሁ (፪x)