Loading
Singer
ችግር ፡ መከራዬን ፡ ብሶቴን የምታውቅ፤ የሚረዳኝ ፡ የለም ፡ ከእኔ ፡ አትራቅ ለአንድ ፡ አፍታ ፡ ከልቤ ፡ ይሄንን ፡ ብነግረውን ቀኜን ፡ ያሰረውን ፡ ገመዴን ፡ በጠሰው (፪x) አዝ፦ መፈታቴን ፡ አውጃለሁ ፡ ለጠላቴም ፡ እነግረዋለሁ በበጉ ፡ ፊት ፡ እሆናለሁ ፡ የድል ፡ ዜማን ፡ አዜማለሁ በሕዝቡ ፡ ፊት ፡ አክብሮኛል ፡ ራሴን ፡ በዘይት ፡ ቀብቶኛል አከብረው ፡ ዘንድ ፡ ይገባኛል ፡ አሜን ኃይለኛና ፡ ታላቅ ፡ ነገር ፡ አደርጋለሁ በእውነት ፡ የታመነ ፡ ቤትን ፡ እሰራለሁ ታማኙ ፡ አምላኬ ፡ እንደተናገረው በእርግጥ ፡ አድርጐታል ፡ ስሙን ፡ አከብራለሁ (፪x) አዝ፦ መፈታቴን ፡ አውጃለሁ ፡ ለጠላቴም ፡ እነግረዋለሁ በበጉ ፡ ፊት ፡ እሆናለሁ ፡ የድል ፡ ዜማን ፡ አዜማለሁ በሕዝቡ ፡ ፊት ፡ አክብሮኛል ፡ ራሴን ፡ በዘይት ፡ ቀብቶኛል አከብረው ፡ ዘንድ ፡ ይገባኛል ፡ አሜን ናቡከደነጾር ፡ የተባለው ፡ ንጉሥ ዓይኖቹን ፡ አንስቶ ፡ ከሰራዊት ፡ ቅዱስ ባቢሎንን ፡ አይቶ ፡ በትዕቢት ፡ ታሰረ ለሰባት ፡ ዘመናት ፡ ምድረ ፡ በዳ ፡ ቀረ ዓይኖቹን ፡ አንስቶ ፡ እግዚአብሔርን ፡ ሲያየው ወደ ፡ ቀድሞው ፡ ሕይወት ፡ ለክብር ፡ መለሰው ይህንን ፡ ላደረገው ፡ ለታላቁ ፡ ጌታ ምሥጋናን ፡ እንስጠው ፡ በዕልልታ ፡ በሆታ (፪x) አዝ፦ መፈታቴን ፡ አውጃለሁ ፡ ለጠላቴም ፡ እነግረዋለሁ በበጉ ፡ ፊት ፡ እሆናለሁ ፡ የድል ፡ ዜማን ፡ አዜማለሁ በሕዝቡ ፡ ፊት ፡ አክብሮኛል ፡ ራሴን ፡ በዘይት ፡ ቀብቶኛል አከብረው ፡ ዘንድ ፡ ይገባኛል ፡ አሜን እስራትን ፡ ፈቶ ፡ ቀንበር ፡ የሰበረ በሰማይ ፡ በምድር ፡ በጣም ፡ የከበረ ፍጥረታት ፡ በሙሉ ፡ ሚታዘዙለት ለበጉ ፡ ለኢየሱስ ፡ ክብር ፡ ይሁንለት (፪x) አዝ፦ መፈታቴን ፡ አውጃለሁ ፡ ለጠላቴም ፡ እነግረዋለሁ በበጉ ፡ ፊት ፡ እሆናለሁ ፡ የድል ፡ ዜማን ፡ አዜማለሁ በሕዝቡ ፡ ፊት ፡ አክብሮኛል ፡ ራሴን ፡ በዘይት ፡ ቀብቶኛል አከብረው ፡ ዘንድ ፡ ይገባኛል ፡ አሜን (፪x)