Loading
Singer
አዝ፦ ምድረበዳው ፡ ተዐምር ፡ መሥሪያ ፡ ነው ፣ ባዶ ፡ ነገር ፡ ሙላትን ፡ ያያል ፤ ሰው ፡ አለቀ ፡ አበቃ ፡ ሲል ፣ የአንተ ፡ ተዐምር ፡ ይጀምራል ። አየሁ ፡ በዐይኔ ፡ የአንተን ፡ በጐነት ፣ በቀን ፡ በሌት ፡ ክንድህ ፡ ሲረዳኝ ፤ በማዕበሉ ፡ በወጀቡ ፡ ላይ ፣ ከፊት ፡ ቀድመህ ፡ በድል ፡ ስትመራኝ ። (፪x) አይቼሃለሁ ፡ ከወዳጅ ፡ ይልቅ ፡ ወዳጅ ፡ የሆንከኝ አይቼሃለሁ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ ክብር ፡ ያሳየኸኝ አይቼሃለሁ ፡ ይሆናል ፡ ያልክልኝ ፡ ሆኗል ፡ በሕይወቴ አይቼሃለሁ ፡ ድካሜን ፡ ሽረህ ፡ ሆንከኝ ፡ ጉልበቴ ያሰበውን ፡ ያቀደውን ፡ በሕይወቴ ፡ ፈጸመና ድንቅን ፡ ሰርቶ ፡ አስደነቀኝ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ እንደገና አዲስ ፡ ታሪክ ፡ አዲስ ፡ ምዕራፍ ፡ ጽፎ ፡ ሰጠኝ ፡ ከሰማይ እርሱ ፡ ካለ ፡ ሆነ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የለበት ፡ አዝዥ ፡ ከልካይ በአንተ ፡ መታመኔ ፡ አዋጣኝ ፡ ጌታዬ አላፈርኩብህም ፡ ያዋጣኛል ፡ ብዬ ጠላቴም ፡ ወዳጄ ፡ ግርም ፡ እስከሚለው ይሄው ፡ ተዐምርህን ፡ በዘመኔ ፡ አየሁ (፪x) አዝ፦ ምድረበዳው ፡ ተዐምር ፡ መሥሪያ ፡ ነው ፣ ባዶ ፡ ነገር ፡ ሙላትን ፡ ያያል ፤ ሰው ፡ አለቀ ፡ አበቃ ፡ ሲል ፣ የአንተ ፡ ተዐምር ፡ ይጀምራል ። አየሁ ፡ በዐይኔ ፡ የአንተን ፡ በጐነት ፣ በቀን ፡ በሌት ፡ ክንድህ ፡ ሲረዳኝ ፤ በማዕበሉ ፡ በወጀቡ ፡ ላይ ፣ ከፊት ፡ ቀድመህ ፡ በድል ፡ ስትመራኝ ። (፪x) አይቼሃለሁ ፡ ከወዳጅ ፡ ይልቅ ፡ ወዳጅ ፡ የሆንከኝ አይቼሃለሁ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ ክብር ፡ ያሳየኸኝ አይቼሃለሁ ፡ ይሆናል ፡ ያልክልኝ ፡ ሆኗል ፡ በሕይወቴ አይቼሃለሁ ፡ ድካሜን ፡ ሽረህ ፡ ሆንከኝ ፡ ጉልበቴ በአንተ ፡ እጅ ፡ ነው ፡ ሁሉ ፡ ነገር የሁሉ ፡ ቁልፍ ፡ የአንተ ፡ ብቻ ይሁን ፡ ያልከው ፡ ሲሆንልህ ፡ አይቻለሁ ፡ የለህ ፡ አቻ ሞተውን ፡ ያበቃውን ፡ ቃል ፡ አውጥተህ ፡ ትጥራለህ ተዘጋው ፡ ደጅ ፡ ገብተህ ፡ ሰላምህን ፡ ታውጃለህ በአንተ ፡ መታመኔ ፡ አዋጣኝ ፡ ጌታዬ አላፈርኩብህም ፡ ያዋጣኛል ፡ ብዬ ጠላቴም ፡ ወዳጄ ፡ ግርም ፡ እስከሚለው ይሄው ፡ ተዐምርህን ፡ በዘመኔ ፡ አየሁ (፪x) አዝ፦ ምድረበዳው ፡ ተዐምር ፡ መሥሪያ ፡ ነው ፣ ባዶ ፡ ነገር ፡ ሙላትን ፡ ያያል ፤ ሰው ፡ አለቀ ፡ አበቃ ፡ ሲል ፣ የአንተ ፡ ተዐምር ፡ ይጀምራል ። አየሁ ፡ በዐይኔ ፡ የአንተን ፡ በጐነት ፣ በቀን ፡ በሌት ፡ ክንድህ ፡ ሲረዳኝ ፤ በማዕበሉ ፡ በወጀቡ ፡ ላይ ፣ ከፊት ፡ ቀድመህ ፡ በድል ፡ ስትመራኝ ። (፪x) አይቼሃለሁ ፡ ከወዳጅ ፡ ይልቅ ፡ ወዳጅ ፡ የሆንከኝ አይቼሃለሁ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ ክብር ፡ ያሳየኸኝ አይቼሃለሁ ፡ ይሆናል ፡ ያልክልኝ ፡ ሆኗል ፡ በሕይወቴ አይቼሃለሁ ፡ ድካሜን ፡ ሽረህ ፡ ሆንከኝ ፡ ጉልበቴ