Loading
Singer
ኢየሱስ ፡ መድህኔ የተጎሳቆለልኝ ፡ ለኔ ነፍሴን ፡ ሊያድናት እርሱ ፡ ሆነ ፡ መስዋእት (፪x) ደሙ ፡ ያድናል ፡ ደሙ (፫) የመስቀል ፡ ላይ ፡ ጣሩ ፡ ስቃዩ ፡ ህመሙ ልከፍልው ፡ በማልችልው ፡ እዳ በሞት ፡ ጥሪ ፡ ነፍሴ ፡ ተገዳ ሳዘግም ፡ ወደ ፡ ሲኦል ፡ መንገድ ከሰማይ ፡ ራርቶልኝ ፡ እግዚአብሔ ውድና ፡ አንድ ፡ ልጁን ፡ ላከልኝ በኔ ፡ ፈንታ ፡ እንዲታረድልኝ ሳያቅማማ ፡ መጣ ፡ ኢየሱሴ አመለጠች ፡ ከሲኦል ፡ ነፍሴ አለብኝ ፡ ውለታዉ (፪)የሱስ ፡ የከፈለዉ ብር ፡ ወርቅ ፡ አይደለም ፡ ነፍሱን ፡ ነዉ(፪x) ተጠምቶ ፡ ሲጠጣ ፡ መራራ ሲከፍል ፡ የኔን ፡ ስቃይ ፡ መከራ የሾህ ፡ አክሊል ፡ ጭኖ ፡ በራሱ ሲጨነቅ ፡ እስክታልፍ ፡ ነፍሱ ቀና ፡ ብሎ ፡ ሲያይ ፡ ወደ አባቱ ጨክኖ ፡ አዞረበት ፡ ፊቱን አንገቱን ፡ ደፍቶ ፡ ስለእኔ ተፈጸመ ፡ አለ ፡ መድህኔ ኢየሱስ ፡ መድህኔ የተጎሳቆለልኝ ፡ ለኔ ነፍሴን ፡ ሊያድናት እርሱ ፡ ሆነ ፡ መስዋእት (፪x) ደሙ ፡ ያድናል ፡ ደሙ (፫) የመስቀል ፡ ላይ ፡ ጣሩ ፡ ስቃዩ ፡ ህመሙ ስለምን ፡ ይሆን ፡ ይሄ ፡ ጌታ ያጣጣረው ፡ በዚያ ፡ ጎልጎታ የተሰደበ ፡ የተተፋበት ባልሰራው ፡ ባልፈጸመው ፡ ሃጢያት ለካ ፡ ስለ እኔ ፡ ነው ፡ ቤዛ ነፍሱን ፡ ከፍሎ ፡ ነፍሴን ፡ የገዛ ቃል ፡ የማይገልጸው ፡ ድንቅ ፡ ፍቅሩ ገለጠልኝ ፡ በመስቀል ፡ ጣሩ አለብኝ ፡ ውለታዉ (፪)የሱስ ፡ የከፈለዉ ብር ፡ ወርቅ ፡ አይደለም ፡ ነፍሱን ፡ ነዉ(፪x)