Loading
Singer
መድኃኒቴን ፡ አየዋለሁ ፡ ዓይኖቼ ፡ ተከፍተዋል በደሙና ፡ በስሙ ፡ ስላነጻን ፍፁም ፡ ህይወት ፡ አሁን ፡ አለኝ ፡ በሞቱ ፡ ፈወሰኝ አሮጌው ፡ ልማድ ፡ ከሕይወቴ ፡ ጠፍቷል አዝ:- አምላኬን ፡ ላመስግን ፡ ሥሙንም ፡ ልወድስ ስላፈቀረኝ ፡ በመስቀል ፡ ተሰቅሎ (ሃሌሉያ) በሕይወቴ ፡ ዘመን ፡ ሁሉ ፡ ኢየሱሴን ፡ ልወድስ ለዓለም ፡ ህዝቦች ፡ የፍቅሩን ፡ ወንጌል ፡ ልግለጽ (፪x) ትኩስ ፡ ቀዝቃዛ ፡ ለብ ፡ ያለ ፡ ህይወት ፡ አትመኑ የጌታ ፡ አገልጋይ ፡ እሳት ፡ ነበልባል ፡ ነው በመንፈስ ፡ እሳት ፡ ግላቹህ ፡ እርሱን ፡ አገልግሉ የድሉን ፡ አክሊል ፡ እንድትቀበሉ አዝ:- ፡ አምላኬን ፡ ላመስግን ፡ ሥሙንም ፡ ልወድስ ስላፈቀረኝ ፡ በመስቀል ፡ ተሰቅሎ (ሃሌሉያ) በሕይወቴ ፡ ዘመን ፡ ሁሉ ፡ ኢየሱሴን ፡ ልወድስ ለዓለም ፡ ህዝቦች ፡ የፍቅሩን ፡ ወንጌል ፡ ልግለጽ (፪x) ነፍሴ ፡ አርፋለች ፡ በዙፋንህ ፡ ሥር በጥላህ ፡ እታመናለሁ መፍትሄ ፡ የሌለው ፡ ምንም ፡ ችግር እንደማያገኘኝ ፡ አውቃለሁ ከአንተ ፡ የተሻለ ፡ ጓደኛ ፡ የለኝም ከአንተ ፡ የቀረበ ፡ ዘመድ ፡ አላገኝም ከአንተ ፡ የበለጠ ፡ ምንም ፡ አልመኝም ሆሆሆ ፡ ኢየሱስ ፡ አለልኝ ፡ ምንም ፡ አይጐለኝም (፫x)