Loading
Singer
አዝ፦ መድሃኒቴ ፡ ብዙ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ያረገው (ያረገው) እንደገና ፡ ስሙን ፡ ላክብረው ውለታው ፡ ለእኔ ፡ ብዙ ፡ ነው (፪x) ሰው ፡ ወዳጁን ፡ ቢወድ ፡ ለጥቂቱ ፡ ነው ጥቅሙም ፡ ሲቀር ፡ ፍቅሩም ፡ ቀሪ ፡ ነው እኔ ፡ ግን ፡ ጠላትህ ፡ ሳለሁ ፡ ወደድከኝ በዘለዓለም ፡ ፍቅርህ ፡ ኢየሱስ ፡ አሰብከኝ አዝ፦ መድሃኒቴ ፡ ብዙ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ያረገው (ያረገው) እንደገና ፡ ስሙን ፡ ላክብረው ውለታው ፡ ለእኔ ፡ ብዙ ፡ ነው (፪x) መንገድ ፡ ላይ ፡ ወድቄ ፡ ጠላቴ ፡ አቁስሎኝ ማንም ፡ አልነበረም ፡ ከውድቀት ፡ ያነሳኝ ዘይትን ፡ አፍስሦ ፡ ቁስሎቼን ፡ የቀባኝ እንደ ፡ ኢየሱሴ ፡ የለኝም ፡ አዳኝ አዝ፦ መድሃኒቴ ፡ ብዙ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ያረገው (ያረገው) እንደገና ፡ ስሙን ፡ ላክብረው ውለታው ፡ ለእኔ ፡ ብዙ ፡ ነው (፪x) ድካም ፡ ችግሬን ፡ የምትሸፍንልኝ ምርኩዝ ፡ ድጋፌም ፡ ጋሻም ፡ የሆንከኝ ከእናት ፡ ከአባቴም ፡ የምትበልጥብኝ መድሃኔቴ ፡ ሆይ ፡ ከፍ ፡ በልልኝ አዝ፦ መድሃኒቴ ፡ ብዙ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ያረገው (ያረገው) እንደገና ፡ ስሙን ፡ ላክብረው ውለታው ፡ ለእኔ ፡ ብዙ ፡ ነው (፪x) አንድ ፡ ሁለት ፡ ብዬ ፡ ቁጥር ፡ ብሰጠው ጌታ ፡ ውለታህ ፡ ከልክ ፡ በላይ ፡ ነው እንደ ፡ እኔ ፡ ውለታው ፡ የበዛባችሁ ቅኔን ፡ ተቀኙለት ፡ እልል ፡ ብላችሁ አዝ፦ መድሃኒቴ ፡ ብዙ ፡ ብዙ ፡ ነው (ብዙ ፡ ብዙ ፡ ነው) ለእኔ ፡ ያረገው (ያረገው) እንደገና ፡ ስሙን ፡ ላክብረው (ስሙን ፡ ላክብረው) ውለታው ፡ ለእኔ ፡ ብዙ ፡ ነው (ለእኔ ፡ ብዙ ፡ ነው) (፪x) ዕልልታ!