Loading
Singer
እጅግ ፡ ከሚያስፈራው ፡ ከገሃነም ፡ እሳት መድሃኒት ፡ የሆንከኝ ፡ ነፍሴን ፡ የታደካት ወደ ፡ ውስጤ ፡ ገብተህ ፡ ፈውስን ፡ አግኝቻለሁ ለዘለዓለሙ ፡ ሳልሰጋ ፡እኖራለሁ (፪x) አዝ፦ መድሃኒቴ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ኦሆሆ ፡ ሌላማ ፡ የለኝም ፡ አሃሃ እውነተኛ ፡ አዳኝ ፡ ኦሆሆ ፡ ፈዋሽ ፡ የሆንከኝ ፡ አሃሃ ሌላማ ፡ ሌላማ ፡ ሌላማ ፡ የለኝም (፪x) ሃሌሉያ መከራ ፡ ዙሪያዬን ፡ ሲያስፈራ ፡ ሲከበኝ ቀር ቦ ፡ የነበረ ፡ ወዳጅም ፡ ሲሸሸኝ ያለኝ ፡ የመሰለኝ ፡ ከጄ ፡ ሲጠፋብኝ አልጥልሽም ፡ እኔ ፡ ከአንቺ ፡ ጋር ፡ ነኝ ፡ አልከኝ (፪x) አዝ፦ መድሃኒቴ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ኦሆሆ ፡ ሌላማ ፡ የለኝም ፡ አሃሃ እውነተኛ ፡ አዳኝ ፡ ኦሆሆ ፡ ረዳት ፡ የሆንከኝ ፡ አሃሃ ሌላማ ፡ ሌላማ ፡ ሌላማ ፡ የለኝም (፪x) ሃሌሉያ ዛሬም ፡ ወደፊት ፡ ለሚያስፈልገኝ ማንስ ፡ ሊያበረታ ፡ ማንስ ፡ ሊያግዘኝ ሰላምም ፡ መፍትሔም ፡ መሆን ፡ የሚቻለው እውነተኛ ፡ ተስፋ ፡ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው (፪x) አዝ፦ መድሃኒቴ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ኦሆሆ ፡ ሌላማ ፡ የለኝም ፡ አሃሃ እውነተኛ ፡ አዳኝ ፡ ኦሆሆ ፡ ፈዋሽ ፡ የሆንከኝ ፡ አሃሃ ሌላማ ፡ ሌላማ ፡ ሌላማ ፡ የለኝም (፪x) ሃሌሉያ