Loading
Singer
እግዚአብሔር ፡ አምላክ ፡ እኛን ፡ በመውደዱ በዘለዓለም ፡ ምክሩ ፡ በበጐ ፡ ፈቃዱ ውድ ፡ ልጁን ፡ ልኮ ፡ ከኃጥያት ፡ አዳነን ገንዘቡም ፡ ሊያደርገን ፡ ዋጋ ፡ ከፍሎ ፡ ዋጀን መድኃኒታችን ፡ ከአመፅ ፡ ተቤዠን በደሙ ፡ አንጽቶ ፡ ለእራሱ ፡ ቀደሰን የመንግሥቱም ፡ ወራሽ ፡ ወገን ፡ አደረገን የናዝሬቱ ፡ ኢየሱስ ፡ በፀጋ ፡ ተሞልቶ የእግዚአብሔር ፡ መንፈስ ፡ በኃይል ፡ ተቀብቶ ሕዝቡን ፡ እየፈታ ፡ ዞረ ፡ እየፈወሰ የዲያቢሎስንም ፡ ሥራ ፡ እያፈረሰ የአምላካችን ፡ ማዳን ፡ የታዳጊነቱ ዝናውም ፡ ሲነገር ፡ የኃያልነቱ ጠላት ፡ተቀጥፈዋል፡ ነደደ:መኣቱ። ሊቀ ፡ ካህናቱ ፡ የአይሁድም ፡ አለቆች ሄሮድስ ፡ ጲላጦስ ፡ የዛ ፡ ዘመን ፡ ዳኞች ቢመረምሩትም ፡ በደል ፡ አጡበት ጻድቅ ፡ ነው ፡ ጌታችን ፡ የለውም ፡ ስህተት ነውርና ፡ እድፍ ፡ ነቀፋ ፡ የሌለው መስዋዕት ፡ በመሆን ፡ ስለ ፡ እኛ ፡ የሞተው ቅዱስ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ጌታችን ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ጀርባውን ፡ በጅራፍ ፡ በእጅጉ ፡ ገርፈው እጆቹን ፡ እግሮቹን ፡ በምስማር ፡ ቸንክረው በመስቀል ፡ አዋሉት ፡ እንደ ፡ በደለኛ የነፍሳቸውን ፡ ዋስ ፡ ያን ፡ ታማኝ ፡ እረኛ የሚያደርጉትን ፡ ባለማወቃቸው አብ ፡ ኃጥያታቸውን ፡ እንዳይዝባቸው እርሱ ፡ ግን ፡ ማለደ ፡ ይቅር ፡ እንዲላቸው መተላለፋችን ፡ ተግሳጽ ፡ ውጣታችን ደዌ ፡ ህመማችን ፡ ስቃይ ፡ መከራችን በምህረቱ ፡ አዋጅ ፡ ወደቀ ፡ ከእዳችን በኢየሱስ ፡ ቤዛነት ፡ ተሻረ ፡ ሞታችን በእርሱ ፡ ስላገኘን ፡ ሰላምና ፡ እርካታ ሃዘንን ፡ በደስታ ፡ ዋይታን ፡ በዕልልታ ስለ ፡ ለወጠልን ፡ ይክበር ፡ የእኛ ፡ ጌታ በአንተ ፡ ስላገኘን ፡ ሰላምና ፡ እርካታ ሃዘንን ፡ በደስታ ፡ ዋይታን ፡ በዕልልታ ስለ ፡ ለወጥክልን ፡ ይክበር ፡ የእኛ ፡ ጌታ