Loading
Singer
አዝ፦ ምድር ፡ ሰፊ ፡ ናት ፡ ምን ፡ ያገፋፋናል መነካከሳችን ፡ ያጠፋፋናል (፪x) የፍቅርን ፡ ጌታ ፡ እያመለክን የፍቅርን ፡ ወንጌል ፡ እየሰበክን መኖር ፡ ስንችል ፡ ተዘልለን ጠላት ፡ በዘዴ ፡ ሥራ ፡ ሰጠን ፍቅርን ፡ አሳዶ ፡ ጥልን ፡ አንግሶ በዓለም ፡ መድረክ ፡ ወንድሙን ፡ ከሶ ቢያዜም ፡ ቢጸልይ ፡ እንዳይቀር ፡ ወጉ ማን ፡ ተባረከ ፡ እስኪ ፡ ፈልጉ አዝ፦ ምድር ፡ ሰፊ ፡ ናት ፡ ምን ፡ ያገፋፋናል መነካከሳችን ፡ ያጠፋፋናል (፪x) የራሱን ፡ ሰርቶ ፡ የሌላውን ፡ ሊያፈርስ አንዱ ፡ በሌላው ፡ ከንፈሩን ፡ ሲነክስ ጠላት ፡ ከኋላ ፡ ድንበር ፡ ሲገፋ አርቆ ፡ አሳቢ ፡ አስተዋይ ፡ ጠፋ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ የሞተላቸው በጐቹ ፡ ሁሉ ፡ የእርሱ ፡ ናቸው በማን ፡ ርስት ፡ ነው ፡ የምንጣላው እንመለስ ፡ ፍርድ ፡ አለ ፡ ኋላ አዝ፦ ምድር ፡ ሰፊ ፡ ናት ፡ ምን ፡ ያገፋፋናል መነካከሳችን ፡ ያጠፋፋናል (፪x) በአንድ ፡ ቤት ፡ ማደር ፡ ቢያቅታቸው አብርሃምና ፡ ሎጥ ፡ ቤተሰብ ፡ ናቸው ችለው ፡ የለም ፡ ወይ ፡ ግራ ፡ ቀኝ ፡ መሄድ ከማን ፡ ተማርነው ፡ ወገን ፡ ማሳደድ ለምንኖርባት ፡ ለዚህች ፡ ምድር ተስፋዋ ፡ ማነው ፡ ያለእግዚአብሔር ፍቅርና ፡ ብርሃን ፡ በእኛ ፡ ከጠፋ በቃ ፡ አለቀላት ፡ የላትም ፡ ተስፋ አዝ፦ ምድር ፡ ሰፊ ፡ ናት ፡ ምን ፡ ያገፋፋናል መነካከሳችን ፡ ያጠፋፋናል (፪x) ፍቅር ፡ ርቦናል ፡ ፍቅር ፡ ጠምቶናል ነገር ፡ ክርክር ፡ አንገላቶናል እናንት ፡ አባቶች ፡ ፍቅርን ፡ መግቡ ከተስፋው ፡ አገር ፡ በሰላም ፡ አግቡ አዝ፦ ምድር ፡ ሰፊ ፡ ናት ፡ ምን ፡ ያገፋፋናል መነካከሳችን ፡ ያጠፋፋናል (፪x)