Loading
Singer
እግዚአብሔርም ፡ በሠራዊቱ ፡ ፊት ፡ ድምጹን ፡ ይሰጣል ሰራዊቱም ፡ ይህን ፡ ይመስላል መልካቸው ፡ እንደ ፡ ፈረስ ፡ መልክ ፡ ነው የማንኮራፋቱ ፡ ክብር ፡ የሚያስፈራ ፡ ነው በኮቴው ፡ በሸለቆው ፡ ውስጥ ፡ ይጐደፍራል በፍርሃት ፡ ላይ ፡ ይስቃል ፣ አይደነግጥም ከሰይፍ ፡ ፊቱን ፡ አይመልስም የመለከትን ፡ ድምጽ ፡ ሲሰማ ፡ እሰይ ፡ ይላል ገለባውንም ፡ እንደሚባላ ፡ እንደ ፡ እሳት ፡ ድምጽ ለሰልፍም ፡ እንደተዘጋጀ ፡ ለብርቱ ፡ ሕዝብ ፡ ያኮበኩባል እንደ ፡ ኃያላን ፡ ይሮጣሉ ፡ ከሰልፈኞችም ፡ በቅጥር ፡ ይወጣሉ እንደ ፡ ሌባም ፡ በመስኮት ፡ ይገባሉ እያንዳንዱ ፡ በመንገዱ ፡ ይራመዳል የራሱን ፡ መንገድ ፡ ይጠበጥባል ። ከእነርሱ ፡ የሚያመልጥ ፡ የለም ። ምድሪቱም ፡ ከፊታቸው ፡ የተነሳ ፡ ትናወጣለች ። እነሆ ፡ እንዲህ ፡ ያለ ፡ ሠራዊት ፡ በምድረ ፡ ኢትዮጵያ ፡ ይገለጣል አሜን! ፡ ሃሌሉያ! አዝ፦ ምድር ፡ ጉድ ፡ ፈላባት (፪x) ፡ ሰራዊት ፡ መጣባት ምድር ፡ ጉድ ፡ ፈላባት (፪x) ፡ ሰራዊት ፡ መጣባት ምድር ፡ አለፈላት (፪x) ፡ ሰራዊት ፡ መጣላት ምድር ፡ አለፈላት (፪x) ፡ ሰራዊት ፡ መጣላት ምን ፡ ዓይነት ፡ ሰራዊት ፡ ነው ፡ የመጣው ምን ፡ ዓይነት ፡ ሰራዊት ፡ ነው (፪x) መልኩ ፡ የፈረስ ፡ ሩጫው ፡ የፈረስ አንዴ ፡ ከገባ ፡ የማይመለስ ዓይኑ ፡ የፈረስ ፡ ድፍረት ፡ የፈረስ አንዴ ፡ ከመጣ ፡ የማይመለስ አዝ፦ ምድር ፡ ጉድ ፡ ፈላባት (፪x) ፡ ሰራዊት ፡ መጣባት ምድር ፡ ጉድ ፡ ፈላባት (፪x) ፡ ሰራዊት ፡ መጣባት ምድር ፡ አለፈላት (፪x) ፡ ሰራዊት ፡ መጣላት ምድር ፡ አለፈላት (፪x) ፡ ሰራዊት ፡ መጣላት ምን ፡ ዓይነት ፡ ሰራዊት ፡ ነው ፡ የመጣው ምን ፡ ዓይነት ፡ ሰራዊት ፡ ነው (፪x) አንገቱ ፡ ጋማ ፡ እንደለበሰ ፡ እየጋለበ ፡ እየገሰገሰ ዘው ፡ ብሎ ፡ ገባ ፡ ጦር ፡ ሜደ ፡ መሃል ፈረሱ ፡ እንደሆን ፡ ሰልፍን ፡ ይወዳል ከት ፡ ብሎ ፡ ይስቃል ፡ በፍርሃት ፡ ላይ አይመለሥም ፡ ጦርነት ፡ ሳያይ እርሱ ፡ ግድ ፡ የለው ፡ ጭራሽ ፡ ይሮጣል አይደነግጥ ፡ ኧረ ፡ እሰይ ፡ ይላል ጦርነት ፡ ሽቶት ፡ ደስታ ፡ የሚሞላ ከፈረስ ፡ በቀር ፡ ማን ፡ አለ ፡ ሌላ ልክ ፡ እንደ ፡ ፈረስ ፡ የሚያስፈራ ሰራዊት ፡ መጥቷል ፡ ኃይል ፡ የተሞላ ምድር ፡ ጉድ ፡ ፈላባት (፪x) ፡ ኃያላን ፡ መጡባት ምድር ፡ አለፈላት (፪x) ፡ ሰራዊት ፡ መጣላት ኢትዮጵያ ፡ አለፈላት (፪x) ፡ ኃያላን ፡ መጡላት ኢትዮጵያ ፡ አለፈላት (፪x) ፡ ጌታ ፡ ደረሰላት ምን ፡ ዓይነት ፡ ሰራዊት ፡ ነው ፡ የመጣው ምን ፡ ዓይነት ፡ ሰራዊት ፡ ነው (፪x) እንደ ፡ ብርቱ ፡ ሕዝብ ፡ ያኮበኩባል በሩን ፡ ብትዘጉ ፡ በመስኮት ፡ ይገባል አንዱ ፡ ካንዱ ፡ ጋር ፡ ሳይገፋፋ አንዱ ፡ በሌላው ፡ ሳይገፋፋ መንገዱን ፡ ይዞ ፡ ቀጥ ፡ ብሎ ፡ ይሄዳል በራሱ ፡ መንገድ ፡ ይጠበጥባል በሰልፍ ፡ መሃከል ፡ በፍልሚያው ፡ ስፍራ የራሱን ፡ ወገን ፡ ስለሚያጣራ ተሳስቶ ፡ ረስቶ ፡ በወንድሙ ፡ ላይ አይለውጠውም ፡ ለይቶ ፡ ሳያይ ስለዚህ ፡ መቁሰል ፡ መሰነከካከል በፍፁም ፡ የለም ፡ በእርሱ ፡ መሃከል ምድር ፡ ጉድ ፡ ፈላባት (፪x) ፡ ሰራዊት ፡ መጣባት ምድር ፡ አለፈላት (፪x) ፡ ሰራዊት ፡ መጣላት ኢትዮጵያ ፡ አለፈላት (፪x) ፡ ኢየሱስ ፡ መጣላት ኢትዮጵያ ፡ አለፈላት (፪x) ፡ ምህረት ፡ ወረደላት ምን ፡ ዓይነት ፡ ሰራዊት ፡ ነው ፡ የመጣው ምን ፡ ዓይነት ፡ ሰራዊት ፡ ነው (፪x) ይሄ ፡ ሰራዊት ፡ በሰልፍ ፡ ሲያልፍባት ዘንድሮስ ፡ ጉድ ፡ ነው ፡ ምድር ፡ ፈርዶባት ትናወጣለች ፡ ይህንን ፡ አይታ በተራራው ፡ ላይ ፡ ኮቴውን ፡ ሰምታ በእቅጥቃጤ ፡ ያናውጧቷል እንቆቅልሿን ፡ ይፈቱላታል እስራቷንም ፡ የሚበጣጥስ ሰራዊት ፡ መጥቷል ፡ የሚገሰግስ ባታምነው ፡ እንኪ ፡ አንተም ፡ እኮ ፡ አለህ የዚህ ፡ ሰራዊት ፡ ዋነኛ ፡ አባል ፡ ነህ አታውቂም ፡ እንጂ ፡ አንቺም ፡ እኮ ፡ አለሽ የዚህ ፡ ሰራዊት ፡ ዋነኛ ፡ አባል ፡ ነሽ ምድር ፡ ጉድ ፡ ፈላባት (፪x) ፡ እኛ ፡ መጣንባት ምድር ፡ አለፈላት (፪x) ፡ እኛ ፡ መጣላት ኢትዮጵያ ፡ አለፈላት (፪x) ፡ ሰራዊት ፡ በዛላት ኢትዮጵያ ፡ አለፈላት (፪x) ፡ እኔ ፡ መጣሁላት ምን ፡ ዓይነት ፡ ሰራዊት ፡ ነው ፡ የመጣው ምን ፡ ዓይነት ፡ ሰራዊት ፡ ነው (፪x) እጁን ፡ ሲጭን ፡ ደዌ ፡ ይፈወሳል በስብከታቸው ፡ ሰው ፡ ይመለሳል በትምህርታቸው ፡ የስህተት ፡ ትምህርት ሊነቀል ፡ ??? ፡ ከስር ፡ ከመሰረት ዝማሬንማ ፡ ከጀማመሩ ፡ መናፍስቶችን ፡ ያራውጣሉ ጌታ ፡ መድሃኒት ፡ ስላደረጋቸው ለምድሪቱ ፡ ፈውስ ፡ መፍትሄ ፡ አላቸው ተረኛ ፡ አድርጐ ፡ ስለላካቸው ለሰራተኞች ፡ ልቀቁላቸው እኛ ፡ እንቢ ፡ ብንል ፡ ሊሆን ፡ ግድ ፡ ነው የሰራዊቱ ፡ መሪ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው ምድር ፡ ጉድ ፡ ፈላባት (፪x) ፡ ሰራዊት ፡ መጣባት ምድር ፡ አለፈላት (፪x) ፡ ኃይለኞች ፡ መጡላት ምድሬ ፡ አለፈላት (፪x) ፡ ጌታዬ ፡ ጐበኛት ምድሬ ፡ አለፈላት (፪x) ፡ ሰራዊት ፡ መጣላት ምን ፡ ዓይነት ፡ ሰራዊት ፡ ነው ፡ የመጣው ምን ፡ ዓይነት ፡ ሰራዊት ፡ ነው (፪x) አላማቸውን ፡ ለገንዘብ ፡ ሲሉ ፡ ለጥቅማጥቅም ፡ የማይደለሉ ለያዙት ፡ እውነት ፡ ቆራጦች ፡ ናቸው በፍፁም ፡ የለም ፡ የሚያስፈራቸው ውስጣቸው ፡ በቃል ፡ ስለተሞሉ ስራ ፡ እያላቸው ፡ ቁጭ ፡ የማይሉ ቀልድና ፡ ተረት ፡ የማያወሩ የሚሯሯጡ ፡ ወደ ፡ መከሩ እነዚህ ፡ ናቸው ፡ ሰራተኞቹ ለእግዚአብሔር ፡ ስራ ፡ ልብ ፡ አድርሶቹ እነኛዎቹም ፡ አበቃላቸው ፡ ሰራዊቶቹን ፡ ጌታ ፡ አስነሳቸው ምድር ፡ ጉድ ፡ ፈላባት (፪x) ፡ ቆራጦች ፡ መጡባት ምድር ፡ አለፈላት (፪x) ፡ ጌታ ፡ ሰው ፡ ላከላት ኢትዮጵያ ፡ አለፈላት (፪x) ፡ መፍትሄ ፡ ተገኘላት ኢትዮጵያ ፡ አለፈላት (፪x) ፡ ኃይለኞች ፡ መጡላት ማነው ፡ የሰራዊቱ ፡ አለቃ ማነው ፡ የሰራዊቱ (፪x) የሰራዊቱ ፡ ዋና ፡ አለቃ ጌታ ፡ እግዚአብሔር ፡ ትዕዛዝ ፡ አወጣ ከፈተላቸው ፡ የምድሪቱን ፡ በር ያለውን ፡ እርግማን ፡ እስኪሰባበር እነርሱም ፡ ቆራጥ ፡ ወሳኞች ፡ ናቸው የተሰማሩ ፡ በየድርሻቸው ውስጣቸው ፡ ፀጋ ፡ ስለተሞሉ ሲጠባበቁ ፡ እስካሁን ፡ አሉ ከእግዚአብሔር ፡ አብ ፡ እንኳን ፡ ቃል ፡ ወጥቶ ተቁነጥኗል ፡ ውስጣቸው ፡ ሞልቶ የልቡን ፡ ሃሳብ ፡ ሊፈጽሙ ፡ ነው ዞር ፡ በሉላቸው ፡ ጊዜው ፡ የእነርሱ ፡ ነው ምድር ፡ ጉድ ፡ ፈላባት (፪x) ፡ ሰራዊት ፡ መጣባት ምድር ፡ ጉድ ፡ ፈላባት (፪x) ፡ ወሳኞች ፡ መጡባት ኢትዮጵያ ፡ አለፈላት (፪x) ፡ ልፍስፍስ ፡ ጠፋላት ኢትዮጵያ ፡ አለፈላት (፪x) ፡ ወሳኞች ፡ መጡላት "መጽሐፍ ፡ ቅዱስ ፡ ጥቅስ"