Loading
Singer
አዝ፦ መዳኔ ፡ ይገርመኛል (፫x) ታምር ፡ ያሰኘኛል (፪x) ከዚህ ፡ በላይ ፡ ታምር ፡ ምንድን ፡ ነው ፡ ሲዖል ፡ ሲዘጋ ከዚህ ፡ በላይ ፡ ታምር ፡ ምንድን ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ሲነጋ ከዚህ ፡ በላይ ፡ ታምር ፡ ምንድን ፡ ነው ፡ ከእስር ፡ ስፈታ ከዚህ ፡ በላይ ፡ ታምር ፡ ምንድን ፡ ነው ፡ ጠላት ፡ ሲመታ (፪x) ጠላት ፡ ሲመታ (፰x) ጨለማው ፡ ሲገፈፍ ፡ ብርሃን ፡ ሲበራ (፪x) አልቆ ፡ ተፈጽሞ ፡ ነገሬ ፡ ሲሰራ (፪x) በዚያ ፡ የመስቀል ፡ ደም ፡ ሰላም ፡ ሲደረግ (፪x) እዳዬን ፡ ስከፍለው ፡ የእግዚአብሔር ፡ በግ (፪x) እግዚአብሔር ፡ ሲዋጋ (፫x) ዘንዶ ፡ ተገደለ ፡ ጠላቴ ፡ ተወጋ ነገር ፡ ተገልብጦ ፡ እኔ ፡ ሰፈር ፡ ነጋ (፪x) አዝ፦ መዳኔ ፡ ይገርመኛል (፫x) ታምር ፡ ያሰኘኛል (፪x) ከዚህ ፡ በላይ ፡ ታምር ፡ ምንድን ፡ ነው ፡ ሲኦል ፡ ሲዘጋ ከዚህ ፡ በላይ ፡ ታምር ፡ ምንድን ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ሲነጋ ከዚህ ፡ በላይ ፡ ታምር ፡ ምንድን ፡ ነው ፡ ከእስር ፡ ስፈታ ከዚህ ፡ በላይ ፡ ታምር ፡ ምንድን ፡ ነው ፡ ጠላት ፡ ሲመታ (፪x) ጠላት ፡ ሲመታ (፰x) አትሞቺም ፡ ብሎ ፡ ሞቴን ፡ ገደለና (፪x) በሕይወት ፡ አኖረኝ ፡ ኪዳኑን ፡ አጸና (፪x) ያ ፡ ባለጋራዬም ፡ ዕቅዱ ፡ ፈረሰ (፪x) እግዚአብሔር ፡ በኢየሱስ ፡ ዕንባዬን ፡ አበሰ (፪x) እግዚአብሔር ፡ ተነሳ (፫x) መከራዬን ፡ ወስዶ ፡ ሀዘኔን ፡ አስረሳ መታሰቢያ ፡ አረገ ፡ ሥሙን ፡ እንዳልረሳ (፪x) አዝ፦ መዳኔ ፡ ይገርመኛል (፫x) ታምር ፡ ያሰኘኛል (፪x) ከዚህ ፡ በላይ ፡ ታምር ፡ ምንድን ፡ ነው ፡ ሲኦል ፡ ሲዘጋ ከዚህ ፡ በላይ ፡ ታምር ፡ ምንድን ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ሲነጋ ከዚህ ፡ በላይ ፡ ታምር ፡ ምንድን ፡ ነው ፡ ከእስር ፡ ስፈታ ከዚህ ፡ በላይ ፡ ታምር ፡ ምንድን ፡ ነው ፡ ጠላት ፡ ሲመታ (፪x) ጠላት ፡ ሲመታ (፰x)