Loading
Singer
አዝ፦ ለእኛስ ፡ ከሌላ ፡ ስፍራ ፡ መዳን ፡ ይሆንልናል (፪x) በዓለም ፡ ምናምን ፡ ተስፋ ፡ አድርገን ልባችን ፡ ረግቶ ፡ እፎይ ፡ ብለን መኖር ፡ እንድንችል ፡ ብዙ ፡ ረባን ሁሉ ፡ ግን ፡ ደቆ ፡ ኢየሱስ ፡ ቀረን አዝ፦ ለእኛስ ፡ ከሌላ ፡ ስፍራ ፡ መዳን ፡ ይሆንልናል (፪x) ወደ ፡ ተራራው ፡ በሮ ፡ ዓይናችን ሊያገኝ ፡ ሮጦ ፡ መድሃኒትን ሲማትር ፡ ከርሞ ፡ ወንዝ ፡ ሜዳውን ኋላ ፡ ቆይ ፡ አለ ፡ ሲያይ ፡ እግዚአብሔርን አዝ፦ ለእኛስ ፡ ከሌላ ፡ ስፍራ ፡ መዳን ፡ ይሆንልናል (፪x) ዛፉን ፡ ቅጠሉን ፡ እንስሳውን ኃይለኛ ፡ አዋቂን ፡ ባለጸጋን ጥበብና ፡ ዕውቀት ፡ ፍልስፍናን ተስፋ ፡ ያደረግን ፡ ሞትን ፡ ተጐዳን አዝ፦ ለእኛስ ፡ ከሌላ ፡ ስፍራ ፡ መዳን ፡ ይሆንልናል (፪x) ኋላ ፡ መለስ ፡ አልን ፡ ሮጠን ፡ ሮጠን በሙላት ፡ ጋበዝን ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታን ካለሰብንበት ፡ መልስ ፡ አገኘን ለዘለዓለም ፡ ክብር ፡ ይሁን አዝ፦ ለእኛስ ፡ ከሌላ ፡ ስፍራ ፡ መዳን ፡ ይሆንልናል (፫x)