Loading
Singer
አዝ፦ መቼም ፡ መቼም ፡ መቼም ፡ አይተወኝ (፪x) ሸምበቆ ፡ አይደል ፡ ስደገፈው ፡ ሚያንሸራትተኝ መቼም ፡ አይተወኝ መቼም ፡ መቼም ፡ መቼም ፡ አይረሳኝ (፪x) ሰው ፡ አይደል ፡ መንገድ ፡ ላይ ፡ ጥሎ ፡ ግራ ፡ የሚያጋባኝ መቼም ፡ አይረሳኝ መቼም ፡ አይተወኝ ፡ መቼም ፡ አይረሳኝ መቼም ፡ አይተወኝ ፡ ገንዘብ ፡ እኮ ፡ ነኝ (፪x) ከእናቴ ፡ ማህጸን ፡ ገና ፡ ገና ፡ ሳለሁኝ እዛው ፡ ውስጥ ፡ እያለሁኝ ፡ ነው ፡ እኮ ፡ በስም ፡ ያወቀኝ የጸጉሬ ፡ ልክ ፡ እንኳን ፡ በእርሱ ፡ የተቆጠረ ፡ ነው ኧረ ፡ እግዚአብሔር ፡ አይተወኝም ፡ ኪዳኑ ፡ ጽኑ ፡ ነው ዝም ፡ ብዬ ፡ ላምልከው ፡ ጐልያድን ፡ ሳልፈራው ዝም ፡ ብዬ ፡ ላምልከው ፡ ዮርዳኖስን ፡ ሳልሰማው ጌታ ፡ በስራ ፡ ላይ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ በስራ ፡ ላይ ሸለቆዬን ፡ ይሞላዋል ፡ ደመናም ፡ ሳላይ በእኔ ፡ ሳይሆን ፡ በእርሱ ፡ ሰዓት ፡ ተራምዶ ፡ ይደርሳል ነገሬን ፡ በብዙ ፡ ክብር ፡ ሰርቶ ፡ ይጨርሳል አዝ፦ መቼም ፡ መቼም ፡ መቼም ፡ አይተወኝ (፪x) ሸምበቆ ፡ አይደል ፡ ስደገፈው ፡ ሚያንሸራትተኝ መቼም ፡ አይተወኝ መቼም ፡ መቼም ፡ መቼም ፡ አይረሳኝ (፪x) ሰው ፡ አይደል ፡ መንገድ ፡ ላይ ፡ ጥሎ ፡ ግራ ፡ የሚያጋባኝ መቼም ፡ አይረሳኝ መቼም ፡ አይተወኝ ፡ መቼም ፡ አይረሳኝ መቼም ፡ አይተወኝ ፡ ገንዘብ ፡ እኮ ፡ ነኝ (፪x) የሠማያት ፡ ወፎች ፡ እንኳን ፡ ሳይዘሩ ፡ ሳያጭዱ ይኸው ፡ ይኖሩ ፡ የለም ፡ ወይ ፡ በእርሱ ፡ እየተረዱ ይልቁንስ ፡ እኔ ፡ ደግሞ ፡ በደም ፡ ተገዝቼ እንዴት ፡ ልፍራ ፡ እንዴት ፡ ልሸበር ፡ ከክፉ ፡ ገብቼ ዝም ፡ ብዬ ፡ ላምልከው ፡ ጐልያድን ፡ ሳልፈራው ዝም ፡ ብዬ ፡ ላምልከው ፡ ዮርዳኖስን ፡ ሳልሰማው ጌታ ፡ በስራ ፡ ላይ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ በስራ ፡ ላይ ሸለቆዬን ፡ ይሞላዋል ፡ ደመናንም ፡ ሳላይ በእኔ ፡ ሳይሆን ፡ በእርሱ ፡ ሰዓት ፡ ተራምዶ ፡ ይደርሳል ነገሬን ፡ በብዙ ፡ ክብር ፡ ሰርቶ ፡ ይጨርሳል ጨለማው ፡ ሲመስል ፡ በእርሱ ፡ ዘንድ ፡ አይጨልምበትም አሃሃሃሃ ፡ አይጨልምበትም ነገሬን ፡ ሊሰራ ፡ ነው ፡ እንጂ ፡ ጌታ ፡ በውበት አሃሃሃሃ ፡ ጌታ ፡ በውበት የሰዎችን ፡ ልጆች ፡ ከልቡ ፡ መቼ ፡ ያስጨንቅና አሃሃሃሃ ፡ መቼ ፡ ያስጨንቅና ዘመናት ፡ ያመጣል ፡ ሊምላ ፡ አፉን ፡ በምሥጋና አሃሃሃ ፡ አፉን ፡ በምሥጋና ከፍ ፡ አደርገዋለሁ ፡ ከፍ ፡ አደርገዋለሁ የርስቴ ፡ ጌታ ፡ ደራሼ ፡ እርሱ ፡ ነው (፬x) ከፍ ፡ አደርገዋለሁ ፡ ከፍ ፡ አደርገዋለሁ የርስቴ ፡ ጌታ ፡ ደራሼ ፡ እርሱ ፡ ነው (፬x)