Loading
Singer
ምሥጋና ፡ ይሞላ ፡ ሁልጊዜ ፡ አንደበቴ ለጸሎት ፡ ይንበርከክ ፡ እስኪዝል ፡ ጉልበቴ አፌም ፡ ይንቀሳቀስ ፡ ያውራ ፡ ስራህን ምላሴም ፡ ይናገር ፡ ይበል ፡ ክብርህን (፪x) አዝ፦ መቼ ፡ ዝም ፡ ያሰኛል ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ውለታህ ለእኔ ፡ ያደረከው ፡ ድንቅ ፡ ተዓምራትህ ኦ ፡ ድንቅ ፡ ተዓምራትህ (፪x) አጽናናህ ፡ አበረታህ ፡ ቁርጭምጪሚቴን እየሮጥኩኝ ፡ ላውራ ፡ ሜዳ ፡ ዳገቱን ይህ ፡ የመዳን ፡ ወንጌል ፡ ለዓለም ፡ ይዳረስ በሠማያዊው ፡ ጠል ፡ ነፍስ ፡ ሁሉ ፡ ይረስርስ (፪x) አዝ፦ መቼ ፡ ዝም ፡ ያሰኛል ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ውለታህ ለእኔ ፡ ያደረከው ፡ ድንቅ ፡ ተዓምራትህ ኦ ፡ ድንቅ ፡ ተዓምራትህ (፪x) ላላወቁህ ፡ ሁሉ ፡ ቀርበው ፡ ላልቀመሱ መናገር ፡ እንድችል ፡ ሙላኝ ፡ በመንፈስህ ሕይወቴ ፡ አርክቶህ ፡ ወዳንተ ፡ እስክደርስ ምስክር ፡ አድርገህ ፡ ለክብርህ ፡ አቁመኝ (፪x) አዝ፦ መቼ ፡ ዝም ፡ ያሰኛል ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ውለታህ ለእኔ ፡ ያደረከው ፡ ድንቅ ፡ ተዓምራትህ ኦ ፡ ድንቅ ፡ ተዓምራትህ (፪x)