Loading
Singer
ማለዳ ፡ እየመጣህ ፡ ስታነቃኝ ጆሮዬን ፡ ከፍተህ ፡ ስትናገረኝ በማስተዋል ፡ መንገድ ፡ ስትመራኝ ከሕይወት ፡ ምንጭ ፡ ውኃ ፡ ስታረካኝ ለምልሞ ፡ ነበር ፡ ሕይወቴ እንዲህ ፡ አልዛለም ፡ ጉልበቴ እባክህ ፡ አስበኝ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ መድኃኒቴ አዝ፦ መቼ ፡ ነው ፡ ነቅቼ ፡ ድምጽህን ፡ የምሰማው ለነፍሴ ፡ መጐብኘት ፡ መጽናናቴ ፡ የሚመጣው (፪x) በሌሊት ፡ ስነሳ ፡ ከእንቅልፌ ሥምህ ፡ ነው ፡ የሚመጣው ፡ ፈጥኖ ፡ በአፌ ህመሜን ፡ ለአንተ ፡ እናገራለሁ ድምጽህን ፡ አሰማኝ ፡ እማራለሁ ጌታ ፡ ሆይ ፡ መቃተቴን ፡ ስማ ነፍሴ ፡ እንደዚህ ፡ ተዳክማ እንደ ፡ ምን ፡ ትዘልቃለች ፡ ትካዜን ፡ ተሸክማ አዝ፦ መቼ ፡ ነው ፡ ነቅቼ ፡ ድምጽህን ፡ የምሰማው ለነፍሴ ፡ መጐብኘት ፡ መጽናናቴ ፡ የሚመጣው (፪x) የተወሰነው ፡ ስዓትህ ፡ ሞልቶ የሀዘኑ ፡ ጊዜ ፡ አብቅቶ ድካም ፡ ድንዛዜ ፡ ተወግዶ ኃይልህ ፡ የሚሞላኝ ፡ ከላይ ፡ ወርዶ መቼ ፡ ነው ፡ ደስ ፡ የምሰኘው በጉብኝትህ ፡ የምጽናናው ጉልበት ፡ ተመልሶ ፡ በእግሬ ፡ የምቆመው አዝ፦ መቼ ፡ ነው ፡ ነቅቼ ፡ ድምጽህን ፡ የምሰማው ለነፍሴ ፡ መጐብኘት ፡ መጽናናቴ ፡ የሚመጣው (፪x)