Loading
Singer
አዝ፦ መራመድ ፡ ሲያቅተኝ ፡ በጽድቅ ፡ ጐዳና ነፍሴም ፡ ስትጨነቅ ፡ በኀጢአት ፡ ፈተና ሥጋዬም ፡ ሲረክስ ፡ ጠፍቶ ፡ ህሊናዬ እንደሰው ፡ መች ፡ ተወኝ (፪x) ፡ ጌታዬ ጨክኖ ፡ መች ፡ ተወኝ (፪x) ፡ ጌታዬ መጠቋቆሚያ ፡ ሲያደርገኝ ፡ ሰው ፡ ሁሉ እንግዲህ ፡ ተስፋም ፡ የለው ፡ እያሉ መች ፡ ቀረሁ ፡ ወድቄ ፡ ተሸማቅቄ ከአምላኬ ፡ ጉያ ፡ እንዲያው ፡ ርቄ እንደገና ፡ አረገኝ ፡ ቀና እንደገና ፡ አረገኝ ፡ ቀና (፪x) አዝ፦ መራመድ ፡ ሲያቅተኝ ፡ በጽድቅ ፡ ጐዳና ነፍሴም ፡ ስትጨነቅ ፡ በኀጢአት ፡ ፈተና ሥጋዬም ፡ ሲረክስ ፡ ጠፍቶ ፡ ህሊናዬ እንደሰው ፡ መች ፡ ተወኝ (፪x) ፡ ጌታዬ ጨክኖ ፡ መች ፡ ተወኝ (፪x) ፡ ጌታዬ ምህረትህን ፡ የለመደ ፡ አመለኛ ተው ፡ ቢሉን ፡ የማይሰማ ፡ እልከኛ ብለው ፡ ፈረዱ ፡ በእግዚአብሔር ፡ ፍቅር በቸርነቱ ፡ ብዙ ፡ የተረዱ የራሳቸውን ፡ ምሶሶ ፡ ትተው የሰውን ፡ ጉድፍ ፡ የሚያዩ ፡ አጥርተው (፪x) አዝ፦ መራመድ ፡ ሲያቅተኝ ፡ በጽድቅ ፡ ጐዳና ነፍሴም ፡ ስትጨነቅ ፡ በኀጢአት ፡ ፈተና ሥጋዬም ፡ ሲረክስ ፡ ጠፍቶ ፡ ህሊናዬ እንደሰው ፡ መች ፡ ተወኝ (፪x) ፡ ጌታዬ ጨክኖ ፡ መች ፡ ተወኝ (፪x) ፡ ጌታዬ ይሄ ፡ ነው ፡ ብዬ ፡ የማልጨርሰው ውለታ ፡ አለብኝ (፪x) ፡ ብዙ ፡ የማላውቀው ይሄ ፡ ነው ፡ ብዬ ፡ የማልጨርሰው ውለታ ፡ አለብኝ (፪x) ፡ ብዙ ፡ የማላውቀው