Loading
Singer
ያረፌ ፡ ሰዉ ፡ በጌታ ፡ ላይ ፡ የተመካ ከቶ ፡ አይሰጋም ፡ አያስፈራው ፡ ክረምት ፡ በጋ መቸ ፡ ፈራ ፡ ልቤ ፡ አልደነገጠም ያባቶቼ ፡ አምላክ ፡ መች ፡ ተለወጠ ኪዳኑ ፡ ጽኑ ፡ አይታጠፍም ደሞ እንደልማዴ ፡ አልኩኝ ፡ እርፍ በማለዳ ፡ በምሽቱ ፡ እዘምራለሁ ፡ በቸርነቱ ባንደበተ ፡ ሞልቷል ፡ ምስጋና ፡ በህይወት ፡ መኖረ ፡ በርሱ ፡ ነውና አላልፈውም ፡ ብዬ ፡ ደምድሜ ፡ ነበረ የሞቱንም ፡ አዋጅ ፡ ጌታዬ ፡ ሰባበረ ታምር ፡ በስቶብኛል ፡ የማወራው አለኝ መባረክ ፡ አይደክመውም ፡ መዘመር ፡ አይደክመኝ አገር ፡ ሰላም ፡ ሁሉ ደና ነው ነገሬ ፡ ሁሉ ፡ በርሱ ፡ ነው ፡ ያለው ተዘልዬ ፡ በጥበቃው ፡ ስር እኖራለው ፡ ሳልሸባበር አላልፈውም ፡ ብዬ ፡ ደምድሜ ፡ ነበረ የሞቱንም ፡ አዋጅ ፡ ጌታዬ ፡ ሰባበረ ታምር ፡ በስቶብኛል ፡ የማወራው አለኝ መባረክ ፡ አይደክመውም ፡ መዘመር ፡ አይደክመኝ