Loading
Singer
እጅህ ፡ አላጠረም ፡ ከመስራት ድምጽህ ፡ አልደከምም ፡ ከመጥራት ይልቅ ፡ በበደሌ ፡ ያሳዘንኩህ ፡ እኔ ማስተዋል ፡ ያቃተኝ ፡ በቃልህ ፡ ስትነግረኝ ስለዚህ ፡ አምልኮዬ ፡ ሆነ ፡ አንካሳ አንዳች ፡ ጠብ ፡ አይልም ፡ በስምህ ፡ ብወቅድ ፡ ብነሳ አዝ፦ ማረኝ ፡ ማረኝ ፡ ጌታ ፡ ማረኝ (፪x) ማረኝ ፡ ማረኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ማረኝ የእኔ ፡ ነው ፡ ጠብና ፡ ክርክር ከአንተ ፡ ይልቅ ፡ መፈለግ ፡ የራስ ፡ ክብር የተጋረደ ፡ ነው ፡ በእኔ ፡ ያለው ፡ ብርሀን እንቅፋት ፡ ሆኛለሁ ፡ ስለ ፡ ሌሎች ፡ መዳን ኑሮዬ ፡ ምልክት ፡ የለውም ፡ የአንተነት ሥጋዬ ፡ በርትቶአል ፡ መንፈሴ ፡ ግን ፡ ደክሟል አዝ፦ ማረኝ ፡ ማረኝ ፡ ጌታ ፡ ማረኝ (፪x) ማረኝ ፡ ማረኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ማረኝ አይታዘዝ ፡ ልቤ ፡ ጠማማ ምላሴ ፡ አይደንግጥ ፡ ሲያማ ወገኑን ፡ የማይወድ ፡ ቂመኛ ፡ ልብ ፡ ያለው ትዕቢት ፡ የተሞላ ፡ ከኔ ፡ ሌላ ፡ ማነው የቀደሙወን ፡ ፍቅር ፡ ከጣልኩት ፡ በጣም ፡ ቆይቻለሁ ሰው ፡ ሲያየኝ ፡ የቆምኩኝ ፡ ብመስልም ፡ እኔስ ፡ ወድቂያለሁ አዝ፦ ማረኝ ፡ ማረኝ ፡ ጌታ ፡ ማረኝ (፪x) ማረኝ ፡ ማረኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ማረኝ ሁለንተናዬ ፡ ግልጽ ፡ በፊትህ አንዳች ፡ እንኳን ፡ የለ ፡ ማልነግርህ ከእግርህ ፡ ስር ፡ ወድቃለሁ ፡ እስከነህ ፡ ኃጢያቴ በደምህ ፡ ታመኜ ፡ ዳግም ፡ ለመንፃቴ እባህክ ፡ ስለ ፡ ስምህ ፡ ብለህ ፡ ራራልኝ በቀራንዮ ፡ መስቀል ፡ በከፈልከው ፡ ዋጋ ፡ አስበኝ አዝ፦ ማረኝ ፡ ማረኝ ፡ ጌታ ፡ ማረኝ (፪x) ማረኝ ፡ ማረኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ማረኝ አንደገና ፡ እንደ ፡ አዲስ ፡ ሃይልን ፡ እሞላለሁ አዝ፡- በንስሀ ፡ ፍሬያማ ፡ ህይወት ፡ እኖራለሁ ፀጋህ ፡ ይበዛለኛል ፡ ቃልህ ፡ እበላለሁ መንፈስህን ፡ ጠጥቼ ፡ የልብህ ፡ ሰው ፡ እሆናለሁ