Loading
Singer
"ልባችሁ ፡ አይታወክ ፡ በእግዚአብሔር ፡ እመኑ ፡ በእኔም ፡ ደግሞ ፡ እመኑ ፤ በአባቴ ፡ ቤት ፡ ብዙ ፡ መኖሪያ ፡ አለ ፤ እንዲህስ ፡ ባይሆን ፡ ባልኋቹ ፡ ነበር ፡፡ ስፍራ ፡ አዘጋችላቹህ ፡ ዘንድ ፡ እሄዳለሁና ፤ ሄጄም ፡ ስፍራ ፡ ባዘጋጅላችሁ ፡ እኔ ፡ ባለሁበት ፡ እናንተ ፡ ደግሞ ፡ እንድትሆኑ ፡ ሁለተኛ ፡ እመጣለሁ ፡ ወደ ፡ እኔም ፡ እወስዳችኋለሁ" ያስጨነቀንን ፡ ሁሉ ፡ ደግመን ፡ ልናስበው እንባችንን ፡ ሊያብስ ፡ ሃዘንን ፡ ሊያርቀው ይህንን ፡ ፈራሽ ፡ ሥጋ ፡ በክብር ፡ ሊለውጠው ቀን ፡ ቀጥሯል ፡ እግዚአብሔር ፡ ቃሉን ፡ ሊፈጽመው ይመጣል ፡ ጌታ ፡ ይመጣል ይመጣል ፡ ኢየሱስ ፡ ይመጣል ይመጣል ፡ በክብር ፡ ይመጣል (፪x) ጠላት ፡ ጦር ፡ አውጥቶ ፡ ቢያጥር ፡ ዙሪያችንን ኑሮው ፡ ትግል ፡ ሆኖ ፡ ቢያዝል ፡ ቢያደክመን የጠበቅነው ፡ ኢየሱስ ፡ በክብር ፡ ሲመጣልን እኛም ፡ ከእርሱ ፡ ጋር ፡ አብረን ፡ እንከብራለን ይመጣል ፡ ጌታ ፡ ይመጣል ይመጣል ፡ ኢየሱስ ፡ ይመጣል ይመጣል ፡ በክብር ፡ ይመጣል (፪x) እግዚአብሔር ፡ መለከት ፡ ከሠማይ ፡ ይወርዳል የወጉትም ፡ ሁሉ ፡ በዓይናቸው ፡ ያዩታል በሙታን ፡ ሕያው ፡ ላይ ፡ ሊፈርድ ፡ ይገለጣል የጌታ ፡ ምጻቱ ፡ ጊዜያቱ ፡ ተቃርቧል ማራናታ ፡ ማራናታ ፡ ማራናታ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ቶሎ ፡ ና (፪x) ቃሉን ፡ የሰጠን ፡ የታመነ ፡ ነው በክብር ፡ በአብ ፡ ቀኝ ፡ የተቀመጠው ወላጅ ፡ እንደሌለው ፡ ከቶ ፡ ላይተወን ይመጣል ፡ ኢየሱስ ፡ ሃሌሉያ ፡ እኛን ፡ ሊወስደን (፪x) ማራናታ ፡ ማራናታ ፡ ማራናታ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ቶሎ ፡ ና (፪x)