Loading
Singer
የመምጣትህ ነገር የመጨረሻው የነገርከን ትንቢት እየሆነ ነው ናፍቆቱ አስባለኝ አሜን ማራናታ ላይህ ጓጉቻለሁ ኢየሱስ የኔ ጌታ ጌታ ኢየሱስ አትመጣም ወይ የደማልኝን ጎንህን ልይ አንተን ለማየት አይኖቼ ሻቱ ቶሎ ናልኝ ኢየሱስ የናዝሬቱ ካንተ ጋር ልዋል ካንተ ጋር ልደር እንደ ዮሐንስ በደረትህ ሥር ደስታ የምለው ትልቁ እርካታዬ አንተ ያለህበት ስኖር ነው ጌታዬ በሌለህበት ከማገኝ ድሎት ምድረበዳ ላይ ካንተ ጋር ልሰንብት አንተን የማየት ናፍቆት ገባብኝ እንደ ጓጓሁኝ መች እቀራለሁኝ ከአመፃ ብዛት ፍቅር ቀዘቀዘ ሰው ወንድሙን ገሎ መቼ ተወቀሰ አመፀኞች በዙ ክፋቱ ጨምሮ ተላልፈው ተሰጡ ለማይረባ አዕምሮ የድሆች ዳኛ የሁሉ አለቃ ና እና ከልክለው ለቅሶአችን ይብቃ የእናቶች እምባ ይላል ዋይ ዋይ ሩህሩህ ጌታ አትመጣም ወይ ቤተ ክርስቲያን ተነሺ እና አብሪ ፍቅርን ለጣሉ እንዳትዘምሪ የገሃነም ደጅ ለካ ጥላቻ ነው ማይቋቋምሽ ሰይፍሽ ፍቅር ሲሆን ነው ጦር መሳሪያውን ፍቅር ያደረገ ጠላቱን ረቶ ወንድም አደረገ የሰው ጠባብ አፍ የሚጎርስ እህል ክፉ አንደበት አክሏል ሲዖል አትመጣም ወይ ማራናታ አናርፍም ወይ ማራናታ (2X) ና ና ና ና ና ማራናታ (4X) ሃሳዊ መምህራን ነብያቶች በዙ ተናገረኝ ባዮች ለገንዘብ የተገዙ ለታመመው ምስኪን እንግዳ ማረፊያ በሽታው ሳያንሰው በፀሎት ሰበብ ዝርፊያ ደምህ ተረግጦ ገንዘብ ገነነ አንተን ያወቀ ሰው ክፉ ሆነ ነዋይ ሚያፈቅር ትውልድ ተነሳ ያረክለትን ምህረት የረሳ ፈውሱ ለታይታ ለንግድ ቀረበ በአዳኙ ስም ገንዘብ ተሰበሰበ ገበያው ደርቶ በወንጌል ሰበብ ስንቱን ታዘብነው አወይ ጉድ አጀብ በሰጠው ፀጋ የሆነ ነጋዴ በፍርድ ቀን የሚል ነው ወይኔ ጉዴ መምጣቱ አይቀርም የእረኞች አለቃ ስለበጎቹ የሚራራ ጠንቃቃ አትመጣም ወይ... ና ና... ወደ ዓለም ሂዱ ወንጌልን ስበኩ ነበር የተባልነው መስክሩ ታደጉ ሰው ግን ካስማ ሰርቶ ወንበሯን ወደደ መምህር እና ጌታ መባልን ለመደ ወንጌል እንስራ አንቱታው ቀርቶ ይሸለም የለ ወይ የሰራ ተግቶ ከታበይንበት ዙፋናችን እስኪ እንውረድ ለጌታችን አላወጣንም አጋንንቶችን አልፈወስንም ወይ በሽተኞችን ጌታ በስምህ ብዙ አድርገን አላውቃችሁም ስለምን አልከን ከሚሉት ወገን እንዳይሆን ሂወቴ መብራቴን ላብራ ሳይጎድል ዘይቴ እስክተመጣልኝ ወይ እስክትወስደኝ እየጠበኩህ እፀናለሁኝ ና ና...