Loading
Singer
በኪሩቤል ፡ ላይ ፡ የተቀመጠው በሰማይ ፡ በምድር ፡ ታላቅ ፡ የሆነው ከዙፋኑ ፡ ላይ ፡ ውረድ ፡ የሚለው እሱን ፡ ተክቶ ፡ የሚቆም ፡ ማነው አዝ፦ ማነው ፡ ማነው ፡ እንዳንተ ፡ ማነው (፪x) ከአምላክ ፡ በቀር ፡ አምላክስ ፡ ማነው ማነው ፡ ማነው ፡ እንዳንተ ፡ ማነው (፪x) ከአንተ ፡ በቀር ፡ አምላክስ ፡ ማነው ውሆች ፡ በእፍኙ ፡ የሰፈረው ሰማይ ፡ በስንዝሩ ፡ የለካው በምን ፡ ምሣሌ ፡ እንመስለው ይህን ፡ እግዚአብሔር ፡ ማን ፡ እንበለው አዝ፦ ማነው ፡ ማነው ፡ እንዳንተ ፡ ማነው (፪x) ከአምላክ ፡ በቀር ፡ አምላክስ ፡ ማነው ማነው ፡ ማነው ፡ እንዳንተ ፡ ማነው (፪x) ከአንተ ፡ በቀር ፡ አምላክስ ፡ ማነው ባህርን ፡ ከፍሎ ፡ የሚያሻግረው ሰማይን ፡ ከፍቶ ፡ መና ፡ የሚያወርደው በጸናች ፡ ክንዱ ፡ የሚታደገው የእስራኤል ፡ አምላክ ፡ እርሱ ፡ ብቻ ፡ ነው አዝ፦ ማነው ፡ ማነው ፡ እንደእርሱ ፡ ማነው (፪x) ከእርሱስ ፡ በቀር ፡ አምላክስ ፡ ማነው ማነው ፡ ማነው ፡ እንዳንተ ፡ ማነው (፪x) ከአንተ ፡ በቀር ፡ አምላክስ ፡ ማነው ክንዱ ፡ አይዝልም ፡ የምናመልከው ሁሌ ፡ ብርቱ ፡ ነው ፡ የማይታክተው ይሄ ፡ አምላካችን ፡ ዛሬም ፡ ሕያው ፡ ነው ተወዳዳሪ ፡ መሳይ ፡ የሌለው አዝ፦ ማነው ፡ ማነው ፡ እንዳንተ ፡ ማነው(፪x) ከአንተ ፡ በቀር ፡ አምላክስ ፡ ማነው ማነው ፡ ማነው ፡ እንደእርሱ ፡ ማነው (፪x) ከእርሱስ ፡ በቀር ፡ አምላክስ ፡ ማነው በነፃ ፡ ብሉ ፡ ጠጡ ፡ የሚለው ዋጋ ፡ ማይጠይቅ ፡ ማያስከፍለው አንድያ ፡ ልጁን ፡ ወዶ ፡ ሚሰጠው ከእግዚአብሔር ፡ በቀር ፡ ወዳጅስ ፡ ማነው አዝ፦ ማነው ፡ ማነው ፡ እንዳንተ ፡ ማነው (፪x) ከአንተ ፡ በቀር ፡ አምላክስ ፡ ማነው ማነው ፡ ማነው ፡ እንዳንተ ፡ ማነው (፪x) ከአንተ ፡ በቀር ፡ ወዳጅስ ፡ ማነው ሁሉን ፡ ይቀርባል ፡ እሩህሩህ ፡ ነው እንደሰው ፡ አይደል ፡ አይሰለቸው ወረትን ፡ አያውቅ ፡ ጊዜ ፡ አይለውጠው እግዚአብሔር ፡ አምላክ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው አዝ፦ ማነው ፡ ማነው ፡ እንዳንተ ፡ ማነው (፪x) ከአምላክ ፡ በቀር ፡ አምላክስ ፡ ማነው ማነው ፡ ማነው ፡ እንዳንተ ፡ ማነው (፪x) ከአንተ ፡ በቀር ፡ አምላክስ ፡ ማነው (፫x)