Loading
Singer
ዳዊት ፡ በዮናታን ፡ ዮናታን ፡ በዳዊት ፍቅር ፡ ሲጀምር ፡ በነገስታት ፡ ቤት በነፍስ ፡ ሲታሰር ፡ የፍቅር ፡ ኪዳን አይለዋወጥ ፡ ፌዝ ፡ የለም ፡ ነበር ሳኦል ፡ ሊገድለው ፡ ሲሻ ፡ ዳዊት ያስመልጥ ፡ ነበር ፡ ቅን ፡ ዮናታን የፍቅር ፡ ትርጉም ፡ ሲገባኝ ፡ እኔ አንድ ፡ አላየሁም ፡ በዚህ ፡ ዘመኔ ትናንት ፡ ሰው ፡ ሲሆን ፡ የወደድኩት ዛሬ ፡ ኣውሬ ፡ ሆኖ ፡ ባይኔ ፡ አየሁት ማታ ፡ በፍቅር ፡ የማለልኝ ጠዋት ፡ ሰማሁት ፡ ሲዝትብኝ ሲለዋወጥስ ፡ የጉራማይሌ እጅጉን ፡ አዘንኩ ፡ ሲረሳ ፡ አምላኬ አዬ ፡ ክርስትናዬ ማነው ፡ እንደ ፡ ኖህ ፡ ኣለምን ፡ በጽድቁ ፡ የኮነነው ኣንደበቱ ፡ ዝም ፡ ብሎ ፡ ህይወቱ ፡ የሚያወራው በፍርድ ፡ ሚዛን ፡ ላይ ፡ ራሱን ፡ አስቀምጦ ወንድሙን ፡ የሚያርድ ፡ በዝቶአል ፡ ከቃሉ ፡ አብልጦ አታርገው ፡ ባዳ ፡ ኣታርገው ፡ ከንቱ እቀፈው ፡ እንጂ ፡ እንደበፊቱ ደም ፡ የፈሰሰው ፡ ቀራንዮ ፡ ላይ ለዚህ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ አንለያይ አንለያይ! ኧረ ፡ እስኪ ፡ ምን ፡ አልከን ስንበላላ ፡ ስንነካከስ ፡ ስንጨራረስ ፡ ጌታችን ምን ፡ ትለን ፡ ይሆን ፡ እስኪ ፡ ምን ፡ አልከን (፪x) ቀንና ፡ ሌሊት ፡ መልካም ፡ አሳቢ ለክፉ ፡ ነገር ፡ መልሱ ፡ ነው ፡ እምቢ ዘመኑን ፡ ሙሉ ፡ ደግ ፡ እየኖረ ፍቅር ፡ ሰባኪ ፡ ለእውነት ፡ ያደረ ግን ፡ ይገርመኛል ፡ የዚህ ፡ ሰው ፡ ሕይወት ምድር ፡ መከራ ፡ ጭንቅ ፡ የሆነችበት ለእውነት ፡ ባደረ ፡ ምላሹ ፡ ሌላ ምነው ፡ ይሄ ፡ ሰው ፡ ሚገፋው ፡ በዛ አይሳመው ፡ እንጂ ፡ ልክ ፡ እንደ ፡ ይሁዳ ያሴርበታል ፡ ሄዶ ፡ ከጓዳ መንገዱ ፡ ቢመስል ፡ ውሎው ፡ ከጌታ ልቡ ፡ ዴማስ ፡ ነው ፡ ሲገለጥ ፡ ማታ አዬ! ፡ ክርስትናዬ! ዘመኑን ፡ ሙሉ ፡ ቤቱ ፡ አገልግሎ በታማኝነት ፡ አምላኩን ፡ ብሎ ደፋ ፡ ቀና ፡ ሲል ፡ ሰጥቶ ፡ ሕይወቱን ድንገት ፡ ወደቀ ፡ ጥሎ ፡ ብርታቱን በኃይሉ ፡ ጊዜ ፡ ያላነሱት ዛሬ ፡ ሲወድቅ ፡ አስታወሱት ከሰገባቸው ፡ ሰይፋቸው ፡ ወጣ የትናንት ፡ ድካም ፡ ሁሉ ፡ እስኪረሳ እንዳይመለስ ፡ እግዜሩን ፡ ፈርቶ ወንድሙ ፡ ቆሞኣል ፡ ቢላውን ፡ ስሎ ታዲያ ፡ ይሄ ፡ ሰው ፡ እንዴት ፡ ይመለስ ፍርድ ፡ ካልመጣ ፡ ከሰማይ ፡ መቅደስ አዬ! ፡ ክርስትናዬ!!