Loading
Singer
አዝ፦ ማንን ፡ እንደጣለ ፡ ይጥልሀል ማንን ፡ እንደተወ ፡ ይተውሀል ጌታ ፡ አንተን ፡ እጅግ ፡ ይወድሀል ሁሉን ፡ ያደርግ ፡ ዘንድ ፡ ቻይ ፡ ነውና ፡ አምላኬ እጠብቀዋለው ፡ ፊቱ ፡ ተንበርክኬ ፡ አዋጅን ፡ በአዋጅ ፡ ሲሽር ፡ ሰምቻለው እሳትን ፡ በእሳት ፡ ሲያጠፋ ፡ አይቻለው አዝ፦ ማንን ፡ እንደጣለ ፡ ይጥልሀል ማንን ፡ እንደተወ ፡ ይተውሀል ጌታ ፡ አንተን ፡ እጅግ ፡ ይወድሀል የቆሸሸን ፡ ታሪክ ፡ ከማህደር ፡ ያወጣል ልብን ፡ ብቻ ፡ አይደለም ፡ ስምን ፡ ይለውጣል በሰው ፡ የተናቁ ፡ መንገድ ፡ የተጣሉ ብዙዎች ፡ ናቸው ፡ በርሱ ፡ አንቱ ፡ የተባሉ አዝ፦ ማንን ፡ እንደጣለ ፡ ይጥልሀል ማንን ፡ እንደተወ ፡ ይተውሀል ጌታ ፡ አንተን ፡ እጅግ ፡ ይወድሀል ለሰይጣን ፡ ሹክሹክታ ፡ ጆሮህን ፡ አትክፈት ጌታ ፡ ያነሳሀል ፡ ዛሬ ፡ ካለህበት ሁሉም ፡ ነገር ፡ አልፎ ፡ ታሪክ ፡ ታወራለህ ስለክብሩ ፡ ቆመህ ፡ ትመሰክራለህ አዝ፦ ማንን ፡ እንደጣለ ፡ ይጥልሀል ማንን ፡ እንደተወ ፡ ይተውሀል ጌታ ፡ አንተን ፡ እጅግ ፡ ይወድሀል እንደ ፡ አውራ ፡ ጎዳና ፡ ሆነህ ፡ መራገጫ ሁሉም ፡ ለምኞቱ ፡ አርጐህ ፡ መወጣጫ እንደወደክ ፡ አትቀር ፡ እንደተረሳህ ጨው ፡ ነው ፡ የምትሆነው ፡ ጌታ ፡ ሲያነሳህ