Loading
Singer
ማን ፡ ያንከባለው ፡ ይህን ፡ ድንጋይ ብዬ ፡ ስማትር ፡ ታች ፡ ላይ ቀና ፡ ብዬ ፡ እንዳይ ፡ አደረከኝ ለካስ ፡ ተንከባሏል ፡ ያስጨነቀኝ (፪x) አሻቅቦ ፡ ማየት ፡ ከሁኔታ ፡ በላይ አድርጎኛል ፡ ጌታ ፡ ችግርን ፡ እንዳላይ ሻገር ፡ ሻገር ፡ ብሎ ፡ አይኔ ፡ ከሩቅ ፡ አይቶ ያመሰግንሃል ፡ ሁሉን ፡ በአንተ ፡ ረስቶ (፪x) ይኸው (፬x) ጌታ ፡ ተቀበለው ፡ ምሥጋናዬ ፡ ይኸው ጌታ ፡ ተቀበለው ፡ አምልኮዬ ፡ ይኸው (፪x) ጭንቅ ፡ ጥብብ ፡ ወየው ፡ ያልኩበት አንገት ፡ ያስደፋኝ ፡ ያለቀስኩበት ያኔ ፡ ያስፈራራኝ ፡ ልቤን ፡ ያራደው ተንከባለለ ፡ ከፊቴ ፡ ያለው (፪x) አሻቅቦ ፡ ማየት ፡ ከሁኔታ ፡ በላይ አድርጎኛል ፡ ጌታ ፡ ችግርን ፡ እንዳላይ ሻገር ፡ ሻገር ፡ ብሎ ፡ ዓይኔ ፡ ከሩቅ ፡ አይቶ ያመሰግንሃል ፡ ሁሉን ፡ በአንተ ፡ ረስቶ (፪x) ይኸው (፬x) ጌታ ፡ ተቀበለው ፡ ምሥጋናዬ ፡ ይኸው ጌታ ፡ ተቀበለው ፡ አምልኮዬ ፡ ይኸው (፪x)