Loading
Singer
ኢየሱስን ፡ ማን ፡ ትሉታላቹህ ከማንስ ፡ ጋር ፡ ታስተያዩታላቹህ የእኔን ፡ ጌታ ፡ ማን ፡ ትሉታላቹህ ከየትኛው ፡ ታስተያዩታላቹህ እርሱ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ሞትን ፡ የረታ ማኅተሙን ፡ ብቻውን ፡ የፈታ የጌቶቹ ፡ ጌታ ፡ የጌቶቹ ፡ ጌታ (፬x) ብዙዎች ፡ ነበሩ ፡ ኃያል ፡ ነን ፡ ያሉ ዘመን ፡ ሲቀየር ፡ እነርሱ ፡ ግን ፡ የሉ እንዲያው ፡ በነበር ፡ ቀረ ፡ ዝናቸው መቃብር ፡ አሉ ፡ ሞት ፡ ድል ፡ ነስቷቸው ሞተ ፡ አበቃ ፡ አከተመለት እያለ ፡ ሰይጣን ፡ ሲሳለቅበት ሞት ፡ መቼ ፡ ያዘው ፡ ይህን ፡ አንበሳ በሶስተኛው ፡ ቀን ፡ ኢየሱስ ፡ ተነሳ ኢየሱስ ፡ ተነሳ (፬x) ፍጥረት ፡ ይህን ፡ ይስማ ፡ ይታወቅ ፡ እውነቱ ሞትን ፡ ድል ፡ ያረገ ፡ እስኪ ፡ ማነው ፡ ብርቱ መጽሃፉን ፡ ከፍቶ ፡ ማኅተሙን ፡ የፈታ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ አሸናፊ ፡ ጌታ አሸናፊ ፡ ጌታ (፬x) እንደ ፡ ጋለ ፡ ነሃስ ፡ አቤት ፡ እግሮቹ እንዴሳት ፡ ነበርላብ ፡ ናቸው ፡ ዐይኖቹ ደረቱን ፡ በወርቅ ፡ መታጠቂያ ፡ ታጥቆ አለ ፡ ይኖራል ፡ ዘለዓለም ፡ ደምቆ ፊቱ ፡ ከፀሐይ ፡ በላይ ፡ ያበራል ግርማ ፡ ሞገሱ ፡ እጅግ ፡ ያስፈራል ይሄ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ እኔ ፡ የማመልከው ሰምቶ ፡ በእሳት ፡ የሚመልሰው የሚመልሰው (፬x) ጌታ ፡ ነው ፡ አቻ ፡ የሌለው (፬x) አቻ ፡ የሌለው (፬x) በሠማይ ፡ በምድር ፡ ከምድርም ፡ በታች መቼ ፡ ተገኘ ፡ መጽሃፉን ፡ ከፋች ዮሐንስ ፡ ሲያለቅስ ፡ ይህንን ፡ አይቶ አታልቅስ ፡ አለው ፡ መላዕኩ ፡ መጥቶ መጽሃፉን ፡ ሊከፍት ፡ ማኅተሙን ፡ ሊፈታ ጀግና ፡ ተገኝቷል ፡ የጌቶች ፡ ጌታ ከዳዊት ፡ ዘር ፡ ግንድ ፡ ያቆጠቆጠው የይሁዳ ፡ አንበሳ ፡ ሁሉን ፡ ፈታታው ሁሉን ፡ ፈታታው (፬x) ጌታ ፡ ነው ፡ አቻ ፡ የሌለው (፬x) አቻ ፡ የሌለው (፬x)