Loading
Singer
አዝ፦ ማነው ፡ ያነጋው ፡ ሌሊቱን ማነው ፡ ያጠፋው ፡ እሳቱን ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ክንደ ፡ ብርቱ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ክንደ ፡ ብርቱ (፪x) በአንድ ፡ መንገድ ፡ የመጡ ፡ በብዙ ፡ በሺህ ፡ ሲወጡ እየወደቁ ፡ ሲነሱ ፡ ክብርን ፡ ለጌታ ፡ ሲሰጡ የናቀኝ ፡ ሁሉ ፡ ሲያከብረኝ ፡ በክብር ፡ ስሜ ፡ ሲጠራኝ ዕድሜ ፡ ሰጥተኸኝ ፡ አየሁኝ ፡ የአንተ ፡ መሆኔ ፡ አኮራኝ (፪x) አዝ፦ ማነው ፡ ያነጋው ፡ ሌሊቱን ማነው ፡ ያጠፋው ፡ እሳቱን ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ክንደ ፡ ብርቱ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ክንደ ፡ ብርቱ (፪x) ከባቢሎን ፡ ወንዞች ፡ ማዶ ፡ ከምርኮ ፡ ከስር ፡ ከተማ የመውጣት ፡ ነገር ፡ ሲነገር ፡ የነፃነት ፡ ድምፅ ፡ ሲሰማ ደወል ፡ ሲመታ ፡ በድንገት ፡ ኧረ ፡ የማን ፡ልብ ፡ አመነ ምን ፡ ያቅትሃል ፡ ጌታችን ፡ አንተ ፡ ስላልከው ፡ ግን ፡ ሆነ (፪x) አዝ፦ ማነው ፡ ያነጋው ፡ ሌሊቱን ማነው ፡ ያጠፋው ፡ እሳቱን ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ክንደ ፡ ብርቱ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ክንደ ፡ ብርቱ (፪x) በባእድ ፡ ምድር ፡ እያለን ፡ የታመቀውን ፡ እሳት ጌታ ፡ ሊያነደው ፡ ጀመረ ፡ አዲስን ፡ ምእራፍ ፡ ሊከፍት ከዛፍ ፡ ወረደ ፡ ማሲንቆ ፡ ከዛፍ ፡ ወረደ ፡ በገና የፅዮን ፡ ዝማሬ ፡ ልንዘምር ፡ አዲሱን ፡ ቅኔ ፡ ምሥጋና (፪x) አዝ፦ ማነው ፡ ያነጋው ፡ ሌሊቱን ማነው ፡ ያጠፋው ፡ እሳቱን ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ክንደ ፡ ብርቱ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ክንደ ፡ ብርቱ (፪x) እያለቀስን ፡ ወጥተናል ፡ በሃዘን ፡ ዘርን ፡ ዘርተናል በምድር ፡ በሠማይ ፡ መካከል ፡ እንባችንን ፡ ረጭተናል የዜማ ፡ ጊዜ ፡ ደረሰ ፡ ነዶአችንን ፡ ይዘን ፡ መጥተናል በውዳችን ፡ ተደግፈን ፡ ከምድረ ፡ በዳ ፡ ወጥተናል (፪x) አዝ፦ ማነው ፡ ያነጋው ፡ ሌሊቱን ማነው ፡ ያጠፋው ፡ እሳቱን ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ክንደ ፡ ብርቱ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ክንደ ፡ ብርቱ (፪x) ጌታ ፡ ምርኮያችንን ፡ ሲመልስ ፡ ለቅሶ ፡ በመዝሙር ፡ ሲተካ ቃላችን ፡ ውስን ፡ ምድራዊ ፡ ደስታችን ፡ በምን ፡ ይለካ አፋችንን ፡ በሳቅ ፡ ሞላ ፡ አንደበታችን ፡ ምሥጋና ሁሉን ፡ ውብ ፡ አድርጓል ፡ የታሪክ ፡ ጌታ ፡ ነውና (፪x) አዝ፦ ማነው ፡ ያነጋው ፡ ሌሊቱን ማነው ፡ ያጠፋው ፡ እሳቱን ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ክንደ ፡ ብርቱ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ክንደ ፡ ብርቱ (፪x)