Loading
Singer
ዘንዶውን ፡ የወጋህ ፡ እባቡን ፡ የረገጥክ ባህሩን ፡ ሰንጥቀህ ፡ ህዝብህን ፡ ያሻገርክ በክብር ፡ ያረገህ ፡ በክብር ፡ የምትመጣ አንተ ፡ አይደለህም ፡ ወይ ፡ ነፃ ፡ የምታወጣ አንተ ፡ አይደለህም ፡ ወይ አዝ:- ማነው ፡ ማነው ፡ እንደ ፡ እግዚአብሄር ፡ ያለ ፡ ታዳጊዬ ለሚታመኑበት ፡ ተዋጊ የገሃነምን ፡ ዘር ፡ ገርስሷል ከሳሼ ፡ አፍሮ ፡ ተመልሷል (፪x) የእነ ፡ ሲድራቅ ፡ አምላክ ፡ የዳንኤል ፡ ታዳጊ ከእቶን ፡ የምታድን ፡ የአምበሳን ፡ አፍ ፡ ዘጊ በዘመናት ፡ ሁል ፡ ከህዝብህ ፡ ጋር ፡ የቆምክ በከሳሻቸው ፡ ፊት ፡ ልጆችህን ፡ ያስከበርክ አንተ ፡ አይደለህም ፡ ወይ አዝ:- ማነው ፡ ማነው ፡ እንደ ፡ እግዚአብሄር ፡ ያለ ፡ ታዳጊዬ ለሚታመኑበት ፡ ተዋጊ የገሃነምን ፡ ዘር ፡ ገርስሷል ከሳሼ ፡ አፍሮ ፡ ተመልሷል (፪x) ሃያላን ፡ በግርማ ፡ ፈጥነው ፡ ሲሟሽሹ በአክብሮት ፡ በፍርሃት ፡ ከፊቱ ፡ ሲሸሹ መራፉን ፡ ይዘጋል ፡ ፍጥረት ፡ በቀጠሮ ጌታ ፡ ብቻ ፡ ይኖራል ፡ ዘላለም ፡ ተከብሮ(፪) አዝ:- ማነው ፡ ማነው ፡ እንደ ፡ እግዚአብሄር ፡ ያለ ፡ ታዳጊዬ ለሚታመኑበት ፡ ተዋጊ የገሃነምን ፡ ዘር ፡ ገርስሷል ከሳሼ ፡ አፍሮ ፡ ተመልሷል (፪x) ይሄ ፡ ታላቅ ፡ አምላክ ፡ እኛን ፡ ከመረጠን በጸጋው ፡ ሸፍኖ ፡ ህዝቤን ፡ አጅብ ፡ ካለኝ አንተ ፡ ብቻ ፡ አምላክ ፡ ሁንልን ፡ ብለናል ታቦቶቻችንም ፡ በእግርህ ፡ ስር ፡ ጥለናል ለአንተ ፡ ተማርከናል አዝ:- ማነው ፡ ማነው ፡ እንደ ፡ እግዚአብሄር ፡ ያለ ፡ ታዳጊዬ ለሚታመኑበት ፡ ተዋጊ የገሃነምን ፡ ዘር ፡ ገርስሷል ከሳሼ ፡ አፍሮ ፡ ተመልሷል (፪x) ጠላቴ ፡ አፍሮ ፡ ተመልሷል ከሳሼ ፡ አፍሮ ፡ ተመልሷል(፫x)