Loading
Singer
ልከፍለው ፡ የማልችል ፡ ነበረብኝ ፡ ዕዳ ችግሬን ፡ ባዋየው ፡ ማን ፡ እኔን ፡ ሊረዳ ኃጥያተኛ ፡ ብሎኝ ፡ ሁሉም ፡ ተጸየፈኝ እንዲፈረድብኝ ፡ ጠላትም ፡ ከሰሰኝ (፪x) ማነው ፡ የሚያድነኝ ፡ ከእንግዲህ ፡ ብዬ ብቻዬን ፡ ሳለቅስ ፡ አገኘኝ ፡ ጌታዬ ዕዳዬን ፡ ተወልኝ ፡ እንባዬን ፡ አበሰው የሕይወቴን ፡ ቁስል ፡ በቁስሉ ፡ ፈወሰው (፪x) ብዙ ፡ ኃጥያቴ ፡ ተሰርዮልኛል አብዝቼ ፡ እንድወደው ፡ በእርግጥ ፡ ይገባኛል ዋጋው ፡ የከበረ ፡ የሽቶ ፡ መስዋዕት ከደስታ ፡ እንባ ፡ ጋር ፡ ምነው ፡ ባቀርብለት (፪x) ለቅሶዬን ፡ ለደስታ ፡ እርሱ ፡ ከለወጠው ሽቶ ፡ ላፈስለት ፡ ብልቃጡን ፡ ብሰብረው ማነው ፡ ቅር ፡ የሚሰኝ ፡ ጌታዬን ፡ ባከብረው ሃብቴን ፡ ብቻ ፡ ሳይሆን ፡ ሕይወቴን ፡ ብሰጠው (፪x) ማንም ፡ በውድቀቴ ፡ ያላዘነልኝን በምድር ፡ ላይ ፡ ፍፁም ፡ ተስፋ ፡ የሌለኝ ሞቴን ፡ ወደ ፡ ሕይወት ፡ መለሰው ፡ ኢየሱስ ስለፍቅርህ ፡ ብዛት ፡ ሥምህን ፡ ልቀድስ (፪x) ማን ፡ እንዳንተ ፡ ጌታ ፡ ልብን ፡ ሊመረምር ማን ፡ ጠልቆ ፡ ሊረዳ ፡ የሰዎችን ፡ ችግር ዕውቀትህ ፡ የላቀ ፡ መሃሪዬ ፡ ነህ ምሥጋናና ፡ ክብር ፡ ይሁን ፡ ለሥምህ ይሁን ፡ ለሥምህ (፪x) ይሁን ፡ ለሥምህ (፪x)