Loading
Singer
እስኪ ፡ ማን ፡ አፈረ ፡ አንተ ፡ ላይ ፡ ተማምኖ ይባርክሃል ፡ እንጂ ፡ ክፉ ፡ ቀኑን ፡ አልፎ ጭው ፡ ባለ ፡ ለሊት ፡ በሮች ፡ ተዘግተው ኢየሱሴ ፡ ብሎ ፡ ያልዳነ ፡ ሰው ፡ ማነው የእኔ ፡ እግዚአብሄር ፡ ጩኸትን ፡ የሚሰማ የእኔ ፡ እግዚአብሄር ፡ እንባብ ፡ የሚያይ ፡ ነው የእኔ ፡ እግዚአብሄር ፡ ከምድረበዳ ፡ ላይ ምንጭ ፡ ያፈልቃል ፡ ያረካል ፡ ደርሶ ፡ ከላይ ምልክት ፡ ሳይኖት ፡ እድል ፡ ቀዳዳ በንዳዱ ፡ እሳት ፡ በምድረበዳ የሚያረሰርስ ፡ አፍልቆ ፡ ውኃ የሚያለመልም ፡ ደረቅ ፡ በረሃ አርክተህ ፡ ሁሉን ፡ ታስደንቃለህ እንዲያው ፡ በመንገድ ፡ መች ፡ ትጥላለህ የጉብኝት ፡ ቀን ፡ ሰጥተህ ፡ ቀጠሮ ያልደረስክለት ፡ ማነው ፡ የሚኖር ፡ አፍሮ ከቶ ፡ አልነበረም ፡ መቼም ፡ አይኖርም ለተናገርከው ፡ ሳትደርስ ፡ አትቀርም እስኪ ፡ ማን ፡ አፈረ ፡ አንተ ፡ ላይ ፡ ተማምኖ ይባርክሃል ፡ እንጂ ፡ ክፉ ፡ ቀኑን ፡ አልፎ ጭው ፡ ባለ ፡ ለሊት ፡ በሮች ፡ ተዘግተው ኢየሱሴ ፡ ብሎ ፡ ያልዳነ ፡ ሰው ፡ ማነው የእኔ ፡ እግዚአብሄር ፡ ጩኸትን ፡ የሚሰማ የእኔ ፡ እግዚአብሄር ፡ እንባብ ፡ የሚያይ ፡ ነው የእኔ ፡ እግዚአብሄር ፡ ከምድረበዳ ፡ ላይ ምንጭ ፡ ያፈልቃል ፡ ያረካል ፡ ደርሶ ፡ ከላይ ማነው ፡ ጌታውን ፡ ያጣ ፡ ጠብቆ ባዶ ፡ የቀረ ፡ የእጁን ፡ ተነጥቆ ተተረከ ፡ እንጂ ፡ አባትነትህ መች ፡ ተነገረ ፡ ቀጥረህ ፡ መቅረትህ ጥበብ ፡ አይጎልህ ፡ ታስደንቃለህ እንዲያው ፡ በመንገድ ፡ መች ፡ ትጥላለህ የጉብኝት ፡ ቀን ፡ ሰጥተህ ፡ ቀጠሮ ያልደረስክለት ፡ ማነው ፡ የሚኖር ፡ አፍሮ ከቶ ፡ አልነበረም ፡ መቼም ፡ አይኖርም ለተናገርከው ፡ ሳትደርስ ፡ አትቀርም ማንም ፡ የለም ፡ ያፈረ ፡ አንተን ፡ ተማምኖ ማንም ፡ የለም ፡ የወደቀ ፡ አንተን ፡ ጠብቆ