Loading
Singer
ጠላቴ ፡ ብዙ ፡ ብዙ ፡ ይጮሃል ጆሮም ፡ አልሰጠው ፡ ይደክማል ለእኔ ፡ የሆነልኝ ፡ እንደዚህ ፡ ነው የዜማ ፡ ጊዜ ፡ ደርሶ ፡ ወይን ፡ አብቦልኝ ፡ ነው (፪x) በለሱን ፡ የጠበቀ ፡ ፍሬዋን ፡ ይበላል ጌታውን ፡ የጠበቀ ፡ ይከብራል ከአምላኩን ፡ ተማምኖ ፡ የከሰረ ፡ የታል በጊዜው ፡ ሰዓቱ ፡ ሁሉ ፡ አምሮለታል (፪x) ማልጄ ፡ ልነሳ ፡ ከበሮዬን ፡ ላንሣ አምላኬን ፡ ላመስግን ፡ ላሰማ ፡ የድል ፡ ዜማ አስጨናቂው ፡ ለሊት ፡ አልፎልኛል ኢየሱስ ፡ ብርሃኔ ፡ በርቶልኛል (፪x) ውሎ ፡ የማድር ፡ ብሆን ፡ ከንጉሥ ፡ ደጅ ፡ አፍ ክፉ ፡ የሚታሰበ ፡ ከንጉሥ ፡ ወዳጅ ጌታውን ፡ ለጠበቀ ፡ ነገሩ ፡ ተገለበጠ በክፉው ፡ ምክር ፡ ላይ ፡ እግዚአብሔር ፡ ተገለጠ (፪x) ማልጄ ፡ ልነሳ ፡ ከበሮዬን ፡ ላንሣ አምላኬን ፡ ላመስግን ፡ ላሰማ ፡ የድል ፡ ዜማ አስጨናቂው ፡ ለሊት ፡ አልፎልኛል ኢየሱስ ፡ ብርሃኔ ፡ በርቶልኛል (፪x)