Loading
Singer
አዝ:- ማን ፡ እንዳንተ ፡ ይሆናል ማንስ ፡ ልብን ፡ ይረዳል ለእኔስ ፡ ሁሉን ፡ ሆንክልኝ ጌታ ፡ በአንተ ፡ አማረብኝ ማዕረጌ ፡ ነህ ፡ ለዘለዓለም ትምክቴ ፡ ነህ ፡ ለዘለዓለም ጋሻዬ ፡ ነህ ፡ ለዘለዓለም ትምክቴ/ውበቴ ፡ ነህ ፡ ለዘለዓለም (፪x) ያማረብኝ ፡ በአንተ ፡ አሃሃሃ ወግ ፡ ያየሁት ፡ በአንተ ፡ አሃሃሃ ሚስጥሩ ፡ ያልገባው ፡ ጥግ ፡ ሆኖ ፡ ቢተቸኝ ያሰኘውን ፡ ይበል ፡ ኧረ ፡ እኔን ፡ አይረብሸኝ ከርግሮህ ፡ ስር ፡ ወድቂ ፡ አሃሃሃ ፈቅጄ ፡ አመልካለሁ ፡ አሃሃሃ መሸ ፡ ነጋ ፡ አልልም ፡ ኑሮዬ ፡ አምልኮ ፡ ነው አዝ:- ማን ፡ እንዳንተ ፡ ይሆናል ማንስ ፡ ልብን ፡ ይረዳል ለእኔስ ፡ ሁሉን ፡ ሆንክልኝ ጌታ ፡ በአንተ ፡ አማረብኝ ማዕረጌ ፡ ነህ ፡ ለዘለዓለም ትምክቴ ፡ ነህ ፡ ለዘለዓለም ጋሻዬ ፡ ነህ ፡ ለዘለዓለም ትምክቴ/ውበቴ ፡ ነህ ፡ ለዘለዓለም (፪x) ያ ፡ ውድ ፡ መዓዛው ፡ ዙፋንህን ፡ ይክበበው የከበረውን ፡ ሽቶ ፡ ከእግርህ ፡ ስር ፡ ልስበረው ክብሬን ፡ እየጣልኩ ፡ ክብር ፡ እሰጥሃለሁ በሁለንተናዬ ፡ ላመልክህ ፡ ቆርጫለሁ አመልካለሁ ፡ ክብሬን ፡ እየጣለኩ አመልካለሁ ፡ ክብርን ፡ እሰጥሃለሁ አመልካለሁ ፡ የመኖሬ ፡ ትርጉም አመልካለሁ ፡ ሚስጥሩ ፡ በአንተ ፡ ነው (፪x) ማዕረጌ ፡ ነህ ፡ ለዘለዓለም ትምክቴ ፡ ነህ ፡ ለዘለዓለም ጋሻዬ ፡ ነህ ፡ ለዘለዓለም ውበቴ ፡ ነህ ፡ ለዘለዓለም (፪x) አዝ:- ማን ፡ እንዳንተ ፡ ይሆናል ማንስ ፡ ልብን ፡ ይረዳል ለእኔስ ፡ ሁሉን ፡ ሆንክልኝ ጌታ ፡ በአንተ ፡ አማረብኝ ማዕረጌ ፡ ነህ ፡ ለዘለዓለም ትምክቴ ፡ ነህ ፡ ለዘለዓለም ጋሻዬ ፡ ነህ ፡ ለዘለዓለም ትምክቴ/ውበቴ ፡ ነህ ፡ ለዘለዓለም (፪x)