Loading
Singer
ከክፉው ፡ ካስፈሪው ፡ ኢየሱስ ፡ ታድጐኛል ከጨለማ ፡ አውጥቶ ፡ ብርሃን ፡ ሆኖልኛል በጠላቴም ፡ ፊት ፡ ዘይት ፡ ቀብቶኛል ከሳሼን ፡ ጥሎልኝ ፡ እኔን ፡ አክብሮኛል አዝ፦ ማዳኑን ፡ ማዳኑን ፡ አይቻለሁ (፪x) ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ለእኔ ፡ አዳኜ ፡ ነው ጥበቃው ፡ ጥበቃው ፡ በላዬ ፡ ላይ (፪x) ሆኖልኛልና ፡ ከሰማይ በባዕድ ፡ አገር ፡ ወገን ፡ አባት ፡ ሆኖልኛል በአለቆችም ፡ ፊት ፡ ሞገስ ፡ ሆንልኛል ወንዙን ፡ ማዕበሉን ፡ እርሱ ፡ አሳልፎኛል በዚህ ፡ ክፉ ፡ ዘመን ፡ ጥላ ፡ ሆንልኛል አዝ፦ ማዳኑን ፡ ማዳኑን ፡ አይቻለሁ (፪x) ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ለእኔ ፡ አዳኜ ፡ ነው ጥበቃው ፡ ጥበቃው ፡ በላዬ ፡ ላይ (፪x) ሆኖልኛልና ፡ ከሰማይ ሥሙ ፡ እንደሚፈስ ፡ ዘይት ፡ ሆኖልኛል ልቤን ፡ በደስታ ፡ አፌን ፡ በሳቅ ፡ ሞልቷል ሕጉ ፡ ለእግሬ ፡ መብራት ፡ ብርሃን ፡ ሆኖልኛል እንዳልሰናከል ፡ ኢየሱስ ፡ ጠብቆኛል አዝ፦ ማዳኑን ፡ ማዳኑን ፡ አይቻለሁ (፪x) ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ለእኔ ፡ አዳኜ ፡ ነው ጥበቃው ፡ ጥበቃው ፡ በላዬ ፡ ላይ (፪x) ሆኖልኛልና ፡ ከሰማይ ምህረት ፡ ቸርነቱ ፡ ፍቅሩ ፡ እኔን ፡ ከቦኛል የማዳኑ ፡ ሥራ ፡ እጅግ ፡ በዝቶልኛል ስተኛ ፡ ቀስቅሶኝ ፡ ስዝል ፡ ደግፎኛል አለቱ ፡ ኢየሱስ ፡ በእጁ ፡ ይዞኛል አዝ፦ ማዳኑን ፡ ማዳኑን ፡ አይቻለሁ (፪x) ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ለእኔ ፡ አዳኜ ፡ ነው ጥበቃው ፡ ጥበቃው ፡ በላዬ ፡ ላይ (፪x) ሆኖልኛልና ፡ ከሰማይ ለውለታው ፡ ሁሉ ፡ ምን ፡ እመልሳለሁ ባወራው ፡ ባወራው ፡ አያልቅም ፡ ብዙ ፡ ነው በሕይወት ፡ ዘመኔ ፡ ለእርሱ ፡ ዘምራለሁ ተመስገን ፡ እያልኩኝ ፡ እቀኝለታለሁ አዝ፦ ማዳኑን ፡ ማዳኑን ፡ አይቻለሁ (፪x) ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ለእኔ ፡ አዳኜ ፡ ነው ጥበቃው ፡ ጥበቃው ፡ በላዬ ፡ ላይ (፪x) ሆኖልኛልና ፡ ከሰማይ (፪x)