Loading
Singer
ብርሃን ፡ ሆነ ፡ ሌሊቱ ፡ ነጋ አዋጅ ፡ ተሰማኝ ፡ ከአሪያም ፡ የወጣ ጌታ ፡ አላለፈኝ ፡ ገባ ፡ ከቤቴ ልዘምርለት ፡ ሞልቷል ፡ ስለቴ ስራዬን ፡ ሰርቶልኝ ፡ ኧረ ፡ እንዴት ፡ አልዘምር ሁሉን ፡ ለአደረገው ፡ ይሁንለት ፡ ክብር ጠላቴን ፡ ጥሎልኝ ፡ ኧረ ፡ እንዴት ፡ አልዘምር ሁሉን ፡ ለአደረገው ፡ ይሁንለት ፡ ክብር ይሁንለት ፡ ክብር (፰x) እግዚአብሔር ፡ ብቻ ፡ መልካም ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ብቻ ፡ መልካም በክፉ ፡ ቀን ፡ መሸሸጊያ ፡ እንደእርሱ ፡ ያለ ፡ የለም (፪x) እንደእርሱ ፡ ያለ ፡ የለም (፰x) አይልኝ ፡ አይልኝ ፡ ጌታ ፡ ከላይ ፡ ፈረደልኝ የጠላቴን ፡ ዛቻ ፡ ከንቱ ፡ አደረገልኝ (፪x) ፎክሮስ ፡ ነበር ፡ ጠላት ፡ በእኔ ፡ ላይ ጌታ ፡ ገልብጦት ፡ ቆምኩኝ ፡ እራሱ ፡ ላይ ድል ፡ አስለመደኝ ፡ ድል ፡ አየሁ ፡ በዐይኔ አከብረዋለሁ ፡ እርሱ ፡ ነው ፡ ክብሬ እርሱ ፡ ነው ፡ ክብሬ (፰x) ዘመን ፡ መጣልኝ ፡ የመገለጫ ከአለት ፡ ንቃቃት ፡ በክብር ፡ መውጫ የይልፈን ፡ ቃል ፡ ሰጠኝ ፡ ጌታዬ ልውጣ ፡ ልገለጥ ፡ በምሥጋናዬ ስራዬን/ጠላቴን ፡ ሰርቶልኝ ፡ ኧረ ፡ እንዴት ፡ አልዘምር ሁሉን ፡ ላደረገው ፡ ይሁንለት ፡ ክብር (፪x) ይሁንለት ፡ ክብር (ይሁንለት) (፰x)