Loading
Singer
ክብሬን ፡ ሁሉ ፡ ጥዬ ፡ ለአንተ ፡ እሰግዳለሁ የሽቶዬን ፡ ብልቃጥ ፡ በፊትህ ፡ አሰብራለሁ አግርህ ፡ ስር ፡ ወድቄ ፡ አገዛልሃለሁ ላከበርከኝ ፡ ጌታ ፡ ይህም ፡ ሲያንስህ ፡ ነው (፪x) አዝ፦ ሌላ ፡ ቃላት ፡ የለኝም ፡ አንተን ፡ የማከብርበት ግን ፡ አንዲያው ፡ ተመስገን ፡ ልበልህ ፡ በሰጠኸኝ ፡ አንደበት (፪x) በምንስ ፡ ጀምሬ ፡ በምን ፡ ልጨርሰው ጌታ ፡ ውለታህን ፡ በምን ፡ ቃል ፡ ልግለጸው እንዲያው ፡ ዝም ፡ ብዬ ፡ ክብርን ፡ አሰጥሃለሁ በብዙ ፡ ምሥጋና ፡ ፊትህ ፡ እቀርባለሁ (፪x) አዝ፦ ሌላ ፡ ቃላት ፡ የለኝም ፡ አንተን ፡ የማከብርበት ግን ፡ አንዲያው ፡ ተመስገን ፡ ልበልህ ፡ በሰጠኸኝ ፡ አንደበት (፪x) ኧረ ፡ እኔስ ፡ ምህረትህ ፡ እጅግ ፡ በዝቶልኛል ብዙ ፡ ኃጢአቴን ፡ ይቅር ፡ ብለኸኛል በዘመኔ ፡ ሁሉ ፡ ለአንተ ፡ እገዛለሁ በገናዬን ፡ ይዤ ፡ ፊትህ ፡ እዘምራለሁ (፪x) አዝ፦ ሌላ ፡ ቃላት ፡ የለኝም ፡ አንተን ፡ የማከብርበት ግን ፡ አንዲያው ፡ ተመስገን ፡ ልበልህ ፡ በሰጠኸኝ ፡ አንደበት (፪x) እኔም ፡ እንዳከብርህ ፡ አንተ ፡ መርጠኸኛል በሞገስ ፡ ላይ ፡ ሞገስ ፡ ደርበህልኛል ሁልጊዜ ፡ በደስታ ፡ አዜምልሃለሁ ራሴን ፡ ዝቅ ፡ በማድረግ ፡ አንተን ፡ አክብራለሁ (፪x) አዝ፦ ሌላ ፡ ቃላት ፡ የለኝም ፡ አንተን ፡ የማከብርበት ግን ፡ አንዲያው ፡ ተመስገን ፡ ልበልህ ፡ በሰጠኸኝ ፡ አንደበት (፪x)