Loading
Singer
ሌላ ፡ ነገር ፡ ይቅር ፡ ይወራ ፡ ስለ ፡ እርሱ በከበረው ፡ ደሙ ፡ ኃጢአት ፡ መደምሰሱ (፪x) አንተ ፡ አንቺ: ሳይባል ፡ ሁሉም ፡ ሰው ፡ ይመነው ኢየሱስን ፡ ማጣት ፡ ሁሉንም ፡ ማጣት ፡ ነው (፪x) የባህል ፡ እስራት ፡ የኃጢአት ፡ ቁራኛ እስከመቼ ፡ ድረስ ፡ እያለን ፡ መዳኛ ፍርድና ፡ ኩነኔ ፡ ለከደነው ፡ ሁሉ መቃብርን ፡ ከፋች ፡ ኢየሱስ ፡ አለ ፡ በሉ አዝ፦ ትልቅ ፡ ስራ ፡ የተሰጠን ፡ ትልቅ ፡ ስራ ስለኢየሱስ ፡ ሳንታክት ፡ ልናወራ አንድ ፡ መንገድ ፡ አንድ ፡ እውነት ፡ አንድ ፡ ሕይወት የተሰጠን ፡ ከእግዚአብሔር ፡ ከሠማያት የእግዚአብሔርን ፡ ትዕዛዝ ፡ ቃሉን ፡ ስለናቀ በአዳም ፡ መተላለፍ ፡ ሁሉም ፡ ሰው ፡ ወደቀ (፪x) የዓለምን ፡ ኃጢአት ፡ በእንጨት ፡ ሊሸከም ሥጋ ፡ ለብሶ ፡ መጣ ፡ ሁለተኛው ፡ አዳም (፪x) ምርኮኛን ፡ የሚያስለቅቅ ፡ እስራት ፡ የሚያስፈታ ምህረትን ፡ ይዞ ፡ የመጣውን ፡ ጌታ አምኖ ፡ ይቀበለው ፡ የሰው ፡ ዘር ፡ በሙሉ ኢየሱስ ፡ ያድናል ፡ የምስራች ፡ በሉ አዝ፦ ትልቅ ፡ ስራ ፡ የተሰጠን ፡ ትልቅ ፡ ስራ ስለ ፡ ኢየሱስ ፡ ሳንታክት ፡ ልናወራ አንድ ፡ መንገድ ፡ አንድ ፡ እውነት ፡ አንድ ፡ ሕይወት የተሰጠን ፡ ከእግዚአብሔር ፡ ከሠማያት ሰይጣኔ ፡ አገዛዝ ፡ ቀንበሩን ፡ ሲያከብድ የዓለም ፡ እንቆቅልሽ ፡ እየበዛ ፡ ሲሄድ (፪x) ኃያላን ፡ ነገሥታት ፡ ፈላስፎች ፡ ቢሆኑ ሊያድን ፡ የተቻለው ፡ ማነው ፡ ለመሆኑ (፪x) የመዳንን ፡ እራስ ፡ በመስቀል ፡ ፈጽሞ ቤት ፡ ሊያዘጋጅልን ፡ የሄደልን ፡ ቀድሞ በሕያዋን ፡ በሙታን ፡ ሊፈርድ ፡ የሚመጣው የጽዮን ፡ ሙሽራ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው አዝ፦ ትልቅ ፡ ስራ ፡ የተሰጠን ፡ ትልቅ ፡ ስራ ስለ ፡ ኢየሱስ ፡ ሳንታክት ፡ ልናወራ አንድ ፡ መንገድ ፡ አንድ ፡ እውነት ፡ አንድ ፡ ሕይወት የተሰጠን ፡ ከእግዚአብሔር ፡ ከሠማያት